ሮሜ 4:2-5
ሮሜ 4:2-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አብርሃም በሥራው ጸድቆስ ቢሆን ትምክሕት በሆነው ነበር፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም። መጽሐፍስ ምን ይላል? አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት። ለሚሠራ ዋጋው እንደሚገባው እንጂ በለጋስነት እንደ ሰጡት ሆኖ አይቈጠርበትም። ለማይሠራ ግን ኀጢአተናውን በሚያጸድቀው ካመነ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል።
ያጋሩ
ሮሜ 4 ያንብቡሮሜ 4:2-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን ኖሮ፣ የሚመካበት ነበረው፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት መመካት አይችልም። መጽሐፍስ ምን ይላል? “አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።” አንድ ሰው ሥራ ከሠራ ደመወዙ እንደ ስጦታ ሳይሆን እንደ ተገቢ ዋጋው ይቈጠርለታል። ነገር ግን ለማይሠራ፣ ሆኖም ኀጥኡን በሚያጸድቀው ለሚያምን፣ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል።
ያጋሩ
ሮሜ 4 ያንብቡሮሜ 4:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም። መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቍኦጠረለት። ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቍኦጠርለትም፤ ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።
ያጋሩ
ሮሜ 4 ያንብቡ