ሮሜ 3:10-18
ሮሜ 3:10-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ “አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም። አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚሻው የለም። ሁሉም ተባብሮ በደለ፤ በጎ ሥራንም የሚሠራ የለም፤ አንድ ስንኳ ቢሆን የለም። ጕረሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በአንደበታቸውም ሸነገሉ፤ ከከንፈሮቻቸውም በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መራራ ነው፤ መርገምንም የተሞላ ነው። እግሮቻቸውም ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው። በመንገዳቸው ጥፋትና ጕስቍልና አለ። የሰላምን መንገድ አያውቋትም። በዐይኖቻቸውም ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።”
ሮሜ 3:10-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ “ጻድቅ ማንም የለም፤ አንድ እንኳ፤ አስተዋይ የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚሻ አንድም የለም። ሁሉም ተሳስተዋል፤ በአንድነት የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ መልካም የሚያደርግ የለም፤ አንድ እንኳ።” “ጕረሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።” “በከንፈሮቻቸው የእባብ መርዝ አለ።” “አፋቸው ርግማንና ምሬት ሞልቶበታል።” “እግሮቻቸው ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ በመንገዶቻቸው ጥፋትና ጕስቍልና ይገኛሉ፤ የሰላምንም መንገድ አያውቁም።” “በዐይናቸው ፊት ፈሪሀ እግዚአብሔር የለም።”
ሮሜ 3:10-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ ቸርነት የሚያደርግ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም። ጕሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ በመላሳቸውም ሸንግለዋል፤ የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤ አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል፤ እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፤ ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው ይገኛል፥ የሰላምንም መንገድ አያውቁም። በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።
ሮሜ 3:10-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ “አንድ እንኳ ጻድቅ ሰው የለም፤ አንድ እንኳን የለም፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ አንድም የለም። ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤ በአንድነት ሆነው ተሳስተዋል። ደግ ሥራ የሚሠራ አንድ ሰው እንኳ የለም። ሰውን የሚጐዳ ክፉ ቃል ለመናገር አፋቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ፤ የከንፈራቸውም ንግግር እንደ እባብ መርዝ የሚጐዳ ነው፤ አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል። እግራቸው ሰውን ለመግደል የፈጠነ ነው፤ በመንገዳቸው የሚገኘው ጥፋትና ጒስቊልና ነው። የሰላምን መንገድ አያውቁም፤ እግዚአብሔርን ከቶ አይፈሩም።”
ሮሜ 3:10-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ “ጻድቅ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም፤ የሚያስተውል የለም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም፤ ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ መልካም የሚሠራ አንድም የለም፤ አንድ ስንኳ የለም።” “ጉሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም አታለዋል፤” “የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤” “አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቷል፤” “እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፤ ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው ይገኛል፤ የሰላምንም መንገድ አያውቁም።” “በዐይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።”