ሮሜ 3:1-4
ሮሜ 3:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንግዲህ አይሁዳዊ የመባል ትርፉ ምንድን ነው? የግዝረትስ ጥቅምዋ ምንድን ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው፤ ነገር ግን ከዚያ አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃል አደራ ተሰጣቸው። የማያምኑ ቢኖሩስ የእነርሱ አለማመን ሌላውን በእግዚአብሔር እንዳያምን ይከለክላልን? አይከለክልም። መጽሐፍ፥ “በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ፥ በፍርድህም ታሸንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር እውነተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰተና ነውና።
ሮሜ 3:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ታዲያ አይሁዳዊ መሆን ጥቅሙ ምንድን ነው? መገረዝስ ምን ፋይዳ አለው? በየትኛውም መንገድ ጥቅሙ ብዙ ነው፤ ከሁሉ አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃል በዐደራ የተሰጠው ለእነርሱ ነው። አንዳንዶች እምነት ባይኖራቸውስ? የእነርሱ አለማመን የእግዚአብሔርን ታማኝነት ዋጋ ያሳጣዋልን? ከቶ አይሆንም! ይልቅስ እግዚአብሔር እውነተኛ፣ ሰው ሁሉ ግን ሐሰተኛ ይሁን፤ “በቃልህ ትጸድቅ፣ በፍርድም ፊት ረቺ ትሆን ዘንድ” ተብሎ ተጽፏልና።
ሮሜ 3:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው። አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጡአቸው። ታዲያ ምንድር ነው? የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀራልን? እንዲህ አይሁን፤ በቃልህ ትጸድቅ ዘንድ ወደ ፍርድ በገባህም ጊዜ ትረታ ዘንድ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ሰው ሁሉ ውሸተኛ ከሆነ እግዚአብሔር እውነተኛ ይሁን።
ሮሜ 3:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እንግዲህ አይሁዳዊ ከአሕዛብ የሚበልጠው በምንድን ነው? የመገረዝስ ጥቅሙ ምንድን ነው? በእርግጥ አይሁዳዊ መሆን በብዙ መንገድ ብልጫ አለው፤ ዋናው ነገር እግዚአብሔር ቃሉን ለአይሁድ ዐደራ መስጠቱ ነው። ታዲያ፥ ከአይሁድ አንዳንዶቹ ታማኞች ሆነው ባይገኙ፥ የእነርሱ ታማኞች አለመሆን የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀራልን? ከቶ አያስቀርም! “ከቃልህ የተነሣ እውነተኛ ትሆናለህ፤ ባላጋራህንም በፍርድ ትረታለህ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም እግዚአብሔር እውነተኛ ነው።
ሮሜ 3:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እንግዲህ አይሁዳዊው ጥቅሙ ምንድነው? ወይም የመገረዝ ትርፉ ምንድነው? በማንኛውም መንገድ ጥቅሙ ብዙ ነው። አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጣቸው። አንዳንዶች ባያምኑስ? የእነሱ አለማመን የእግዚአብሔርን ታማኝነት ዋጋ የሌለው ያደርገዋልን? በጭራሽ! “በቃልህ እውነተኛ እንድትሆን፥ ለፍርድ በቀረብክም ጊዜ አሸናፊ እንድትሆን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ግን እውነተኛ ይሁን።