ሮሜ 2:1-5

ሮሜ 2:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አንተ ሰው ሆይ፥ እው​ነት ለሚ​ፈ​ር​ደው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለህ? በወ​ን​ድ​ምህ ላይ የም​ት​ጠ​ላ​ውን ያን ሥራ አንተ ራስህ ከሠ​ራ​ኸው በራ​ስህ የም​ት​ፈ​ርድ አይ​ደ​ለ​ምን? አንተ ራስህ ያን ሥራ ትሠ​ራ​ዋ​ለ​ህና። ይህም እን​ደ​ዚህ በሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች ላይ ቅጣት የሚ​ያ​መጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርዱ እው​ነት እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን። አንተ ሰው ሆይ፥ በሌላ ላይ አይ​ተህ የም​ት​ጠ​ላ​ው​ንና የም​ት​ነ​ቅ​ፈ​ውን ያን አንተ ራስህ የም​ት​ሠ​ራው ከሆነ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ እን​ደ​ም​ታ​መ​ልጥ ታስ​ባ​ለ​ህን? ወይስ በቸ​ር​ነቱ ብዛት በመ​ታ​ገሡ፥ ለአ​ን​ተም እሺ በማ​ለቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ዋቂ ልታ​ደ​ር​ገው ታስ​ባ​ለ​ህን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ቸር​ነቱ አን​ተን ወደ ንስሓ እን​ዲ​መ​ል​ስህ አታ​ው​ቅ​ምን? ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።