ሮሜ 16:1-2 - Compare All Versions

ሮሜ 16:1-2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ለክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን የም​ት​ላ​ላ​ከ​ውን እኅ​ታ​ች​ንን ፌቤ​ንን አደራ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለቅ​ዱ​ሳ​ንም እን​ደ​ሚ​ገባ በጌ​ታ​ችን ተቀ​በ​ሉ​አት፤ እር​ስዋ ለብ​ዙ​ዎች፥ ለእ​ኔም ረዳት ናትና፤ ለች​ግ​ራ​ች​ሁም በፈ​ቀ​ዳ​ች​ሁት ቦታ መድ​ቡ​አት።

ሮሜ 16:1-2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በክንክራኦስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነችውን እኅታችንን ፌቤንን ዐደራ እላችኋለሁ። ለቅዱሳን ተገቢ በሆነው አቀባበል በጌታ እንድትቀበሏትና ከእናንተም የምትፈልገውን ማንኛውንም ርዳታ እንድታደርጉላት አሳስባችኋለሁ፤ ለብዙ ሰዎችና ለእኔም ጭምር ታላቅ ድጋፍ ነበረችና።

ሮሜ 16:1-2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በክንክራኦስ ባለች ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የምትሆን እኅታችንን ፌቤንን አደራ ብያችኋለሁ፤ ለቅዱሳን እንደሚገባ በጌታ ተቀበሉአት፥ እርስዋ ለብዙዎች ለእኔም ለራሴ ደጋፊ ነበረችና፥ ከእናንተም በምትፈልገው በማናቸውም ነገር እርዱአት።

ሮሜ 16:1-2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ፌቤ በክንክሪያ ከተማ ቤተ ክርስቲያንን የምታገለግል ታማኝ እኅታችን መሆንዋን እንድታውቁ እወዳለሁ። እርስዋ እኔንና ሌሎችንም ብዙ ሰዎች የረዳች ስለ ሆነች ምእመናን እንግዶችን መቀበል እንደሚገባቸው ዐይነት በጌታ ስም ተቀብላችሁ በሚያስፈልጋት ነገር ሁሉ እንድትረዱአት ዐደራ እላችኋለሁ።

ሮሜ 16:1-2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በኬንክሪየስ ቤተ ክርስቲያን ዲያቆን የሆነችውን እኅታችንን ፊቢንን አደራ ብያችኋለሁ፤ ለቅዱሳን እንደሚገባ በጌታ ተቀአሉአት፤ ከእናንተም በምትፈልገው በማንኛውም ነገር እርዱአት፤ እርሷ ለብዙዎች ለእኔም ጭምር ረድታለችና።