ሮሜ 14:7-9
ሮሜ 14:7-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከመካከላችንም ለራሱ የሚኖር፥ ለራሱም የሚሞት የለም። በሕይወት ብንኖርም ለእግዚአብሔር እንኖራለን፤ ብንሞትም ለእግዚአብሔር እንሞታለን፤ እንግዲህ በሕይወት ብንኖርም ብንሞትም ለእግዚአብሔር ነን። ስለዚህ ሕያዋንንና ሙታንን ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞተ፥ ተነሣም።
ያጋሩ
ሮሜ 14 ያንብቡሮሜ 14:7-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከእኛ ማንም ለራሱ የሚኖር፣ ለራሱም የሚሞት የለምና። ብንኖር ለጌታ እንኖራለን፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። ስለዚህ ብንኖርም ብንሞትም የጌታ ነን። ለዚሁ፣ የሙታንና የሕያዋን ጌታ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ ሞቷል፤ በሕይወትም ተነሥቷል።
ያጋሩ
ሮሜ 14 ያንብቡሮሜ 14:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና፥ ለራሱም የሚሞት የለም፤ በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን። ስለዚህ ነገር ሙታንንም ሕያዋንንም ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞቶአልና ሕያውም ሆኖአልና።
ያጋሩ
ሮሜ 14 ያንብቡ