ሮሜ 14:1-9

ሮሜ 14:1-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እም​ነቱ ደካማ የሆ​ነ​ውን ሰው ታገ​ሡት፤ በዐ​ሳ​ቡም አት​ፍ​ረዱ። ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈ​ቀ​ደ​ለት የሚ​ያ​ምን ሁሉን ይብላ፤ የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን አት​ክ​ልት ይብላ። የሚ​በ​ላ​ውም የማ​ይ​በ​ላ​ውን አይ​ና​ቀው፤ የማ​ይ​በ​ላ​ውም የሚ​በ​ላ​ውን አይ​ን​ቀ​ፈው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አው​ቆ​አ​ቸ​ዋ​ልና። እን​ግ​ዲህ የሌ​ላ​ውን ሎሌ የም​ት​ነ​ቅፍ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወ​ድቅ ለጌ​ታው ነው። ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ነ​ሣው ይች​ላ​ልና ይቆ​ማል። ከቀን ቀን የሚ​ከ​ለ​ከል አለና፤ ዘወ​ት​ርም የሚ​ከ​ለ​ከል አለና፤ ነገር ግን ሁሉም ልቡ እንደ ወደደ ያድ​ርግ። አን​ዳ​ንድ ቀን የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤ ዘወ​ትር የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤ የበ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፤ ያል​በ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​በ​ላም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል። ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ንም ለራሱ የሚ​ኖር፥ ለራ​ሱም የሚ​ሞት የለም። በሕ​ይ​ወት ብን​ኖ​ርም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ኖ​ራ​ለን፤ ብን​ሞ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ግ​ዲህ በሕ​ይ​ወት ብን​ኖ​ርም ብን​ሞ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነን። ስለ​ዚህ ሕያ​ዋ​ን​ንና ሙታ​ንን ይገዛ ዘንድ ክር​ስ​ቶስ ሞተ፥ ተነ​ሣም።

ሮሜ 14:1-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በእምነቱ ደካማ የሆነውን ሰው፣ አከራካሪ በሆኑ ጕዳዮች ላይ በአቋሙ ሳትፈርዱበት ተቀበሉት። የአንድ ሰው እምነቱ ማንኛውንም ነገር እንዲበላ ይፈቅድለታል፤ በእምነቱ ያልጠነከረው ሌላው ሰው ግን አትክልት ብቻ ይበላል። ማንኛውንም የሚበላ የማይበላውን አይናቅ፤ የማይበላውም የሚበላውን አይኰንን፤ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና። ሌላውን በሚያገለግል ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? እርሱ ቢወድቅ ወይም ቢቆም ለጌታው ነው፤ ጌታ ሊያቆመው ስለሚችልም ይቆማል። አንድ ሰው አንዱን ቀን ከሌላው የተሻለ ቅዱስ አድርጎ ይቈጥራል፤ ሌላው ደግሞ ቀኖች ሁሉ እኩል እንደ ሆኑ ያስባል። እያንዳንዱ የራሱን ውሳኔ ልብ ብሎ ይወስን። አንድን ቀን ከሌላው የተለየ አድርጎ የሚያስብ ሰው፣ እንዲህ የሚያደርገው ለጌታ ብሎ ነው፤ ሥጋ የሚበላውም ለጌታ ብሎ ይበላል፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀርባልና። የማይበላም ለጌታ ሲል አይበላም፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ያቀርባል። ከእኛ ማንም ለራሱ የሚኖር፣ ለራሱም የሚሞት የለምና። ብንኖር ለጌታ እንኖራለን፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። ስለዚህ ብንኖርም ብንሞትም የጌታ ነን። ለዚሁ፣ የሙታንና የሕያዋን ጌታ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ ሞቷል፤ በሕይወትም ተነሥቷል።

ሮሜ 14:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ። ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል። የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና። አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል። ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንዲሻል ያስባል፥ ያ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደ ሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ። ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል፤ የሚበላም እግዚአብሔርን ያመሰግናልና ለጌታ ብሎ ይበላል፤ የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም እግዚአብሔርንም ያመሰግናል። ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና፥ ለራሱም የሚሞት የለም፤ በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን። ስለዚህ ነገር ሙታንንም ሕያዋንንም ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞቶአልና ሕያውም ሆኖአልና።

ሮሜ 14:1-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በእናንተ መካከል በእምነቱ ደካማ የሆነውን ሰው ተቀበሉት እንጂ በግል ሐሳቡ ላይ ክርክር አታንሡ። ለምሳሌ አንድ ሰው ማንኛውንም ነገር ለመብላት የሚያስችል እምነት ይኖረዋል፤ በእምነቱ ያልጸናው ሰው ግን አትክልት ብቻ ይበላል፤ ስለዚህ ማንኛውንም ነገር የሚበላ ሰው የማይበላውን ሰው አይንቀፈው፤ የማይበላውም በሚበላው ሰው ላይ አይፍረድ፤ እርሱንም እግዚአብሔር ተቀብሎታልና። ታዲያ፥ በሌላ ሰው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ የጌታው ጉዳይ ነው። እንዲያውም እግዚአብሔር ሊያቆመው ስለሚችል ጸንቶ ይቆማል። እንዲሁም አንዱ ቀን ከሌላው ቀን ይበልጥ ክቡር ነው ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆናል፤ ሌላው ደግሞ ቀኖች ሁሉ እኩል ክብር አላቸው እንጂ በቀኖች መካከል ልዩነት የለም ብሎ ያስባል። እንግዲህ ይህን በመሳሰለው ነገር እያንዳንዱ ሰው ከልቡ ያመነበትን ያድርግ። አንዱን ቀን ከሌላው ቀን አስበልጦ የሚያከብር ቢኖር ይህን ማድረጉ ለጌታ ክብር ብሎ ነው፤ ማንኛውንም ምግብ የሚበላ ለጌታ ክብር ብሎ ይበላል፤ ስለሚበላውም ምግብ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤ ማንኛውንም ምግብ የማይበላ ለጌታ ክብር ብሎ አይበላም፤ ባለመብላቱም እግዚአብሔርን ያመሰግናል። ከእኛ እያንዳንዱ ሕይወቱም ሆነ ሞቱ የራሱ አይደለም። ብንኖር ለጌታ እንኖራለን፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን፤ ስለዚህ ብንኖርም፥ ብንሞትም የጌታ ነን። ስለዚህ ክርስቶስ ሞቶ ከሞት የተነሣው የሕያዋንና የሙታን ጌታ ለመሆን ነው።

ሮሜ 14:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በእምነት የደከመውንም አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሳትፈርዱበት ተቀበሉት። ሁሉን መብላት እንደሚችል የሚያምን አለ፤ በእምነት ደካማው ግን አትክልት ይበላል። የሚበላ የማይበላውን አይናቀው፤ የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፤ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና። አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን ጌታ ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል። ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንደሚሻል ያስባል፤ ሌላው ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ። አንድን ቀን ከሌላው የተለየ አድርጎ የሚያስብ ሰው ለጌታ ብሎ ነው፤ የሚበላም ለጌታ ብሎ ይበላል፤ እግዚአብሔርን ያመሰግናልና የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግናል። ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና፤ ለራሱም የሚሞት የለም፤ በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን። ስለዚህ ነገር የሙታንንና የሕያዋን ጌታ እንዲሆን ክርስቶስ ሞቷልና፥ ሕያውም ሆኖአልና።