ሮሜ 13:3-4
ሮሜ 13:3-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሹሞች ሥራው ክፉ ለሆነ ሰው እንጂ መልካም ለሚሠራ የሚአስፈሩ አይደሉም፤ ሹሞችን እንዳትፈራ ብትፈልግ መልካም አድርግ፤ እነርሱ ደግሞ ያመሰግኑሃል፤ አንተ ሥራህን ታሳምር ዘንድ የእግዚአብሔር መልእክተኞች ናቸውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ ሰይፍ የታጠቁም ለከንቱ አይደለም፤ ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።
ሮሜ 13:3-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ገዦች ክፉ ለሚሠሩ እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትፈልጋለህን? እንግዲያስ መልካሙን አድርግ፤ እርሱም ያመሰግንሃል፤ እርሱ ለአንተ መልካሙን ለማድረግ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። ነገር ግን ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ምክንያቱም ሰይፉን በከንቱ አልታጠቀም፤ ክፉ የሚያደርገውን ለመቅጣት የቍጣ መሣሪያ የሆነ፣ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው።
ሮሜ 13:3-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤ ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።
ሮሜ 13:3-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ገዢዎች የሚያስፈሩት ክፉ አድራጊዎችን እንጂ መልካም አድራጊዎችን አይደለም፤ ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ መልካሙን ነገር አድርግ፤ ከእርሱም ምስጋናን ታገኛለህ። ባለሥልጣን ለአንተ መልካም እንዲያደርግ የተሾመ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፤ ባለሥልጣን ሰይፍ የታጠቀው በከንቱ ስላልሆነ ክፉ አድራጊ ከሆንክ ባለሥልጣንን ፍራ፤ እርሱ ክፉ አድራጊዎችን በመቅጣትና የእግዚአብሔርን በቀል በማሳየት እግዚአብሔርን ያገለግላል።