ሮሜ 13:1-3
ሮሜ 13:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሰው ሁሉ በበላይ ላሉ ባለሥልጣኖች ይገዛ፤ ከእግዚአብሔር ከአልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ለባለሥልጣን አልገዛም ያለ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንቢ ማለቱ ነው፤ መገዛትን እንቢ የሚሉም በራሳቸው ላይ ቅጣትን ያመጣሉ። ሹሞች ሥራው ክፉ ለሆነ ሰው እንጂ መልካም ለሚሠራ የሚአስፈሩ አይደሉም፤ ሹሞችን እንዳትፈራ ብትፈልግ መልካም አድርግ፤ እነርሱ ደግሞ ያመሰግኑሃል፤
ሮሜ 13:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ማንኛውም ሰው በሥልጣን ላሉት ሹማምት መገዛት ይገባዋል፤ ከእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣናት በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ፣ በባለሥልጣን ላይ የሚያምፅ በእግዚአብሔር ሥርዐት ላይ ማመፁ ነው፤ ይህን የሚያደርጉትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ያመጣሉ። ገዦች ክፉ ለሚሠሩ እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትፈልጋለህን? እንግዲያስ መልካሙን አድርግ፤ እርሱም ያመሰግንሃል፤
ሮሜ 13:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤
ሮሜ 13:1-3 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ማንኛውም ሥልጣን የሚገኘው በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ሆነና አሁን ያሉትም ባለሥልጣኖች የተሾሙት በእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ ሰው ሁሉ ለበላይ ባለሥልጣን መታዘዝ አለበት። ስለዚህ ባለሥልጣንን የሚቃወም ሁሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይቃወማል፤ የማይታዘዝም ሁሉ በራሱ ላይ የቅጣትን ፍርድ ያመጣል። ገዢዎች የሚያስፈሩት ክፉ አድራጊዎችን እንጂ መልካም አድራጊዎችን አይደለም፤ ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ መልካሙን ነገር አድርግ፤ ከእርሱም ምስጋናን ታገኛለህ።
ሮሜ 13:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ሁሉም ሰው ለበላይ ባለ ሥልጣናት ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። ገዢዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ፤ ከእርሱም ምስጋናን ታገኛለህ፤