ሮሜ 12:11-19 - Compare All Versions

ሮሜ 12:11-19 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ለሥራ ከመ​ት​ጋት አት​ስ​ነፉ፤ በመ​ን​ፈስ ሕያ​ዋን ሁኑ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ፤ በተ​ስፋ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በመ​ከራ ታገሡ፤ ለጸ​ሎት ትጉ። በች​ግ​ራ​ቸው ቅዱ​ሳ​ንን ለመ​ር​ዳት ተባ​በሩ፤ እን​ግዳ መቀ​በ​ል​ንም አዘ​ው​ትሩ። የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አት​ር​ገሙ። ደስ ከሚ​ለው ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከሚ​ያ​ለ​ቅ​ሰው ጋርም አል​ቅሱ። እርስ በር​ሳ​ች​ሁም በአ​ንድ ዐሳብ ተስ​ማሙ፤ ትዕ​ቢ​ትን ግን አታ​ስቡ፤ ራሱን የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ው​ንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋ​ቆች ነን አት​በሉ። ክፉ ላደ​ረ​ገ​ባ​ች​ሁም ክፉ አት​መ​ል​ሱ​ለት፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ​ውን ተነ​ጋ​ገሩ። ቢቻ​ላ​ች​ሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰ​ላም ኑሩ። ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ራሳ​ችሁ አት​በ​ቀሉ፤ ቍጣን አሳ​ል​ፏት፥ “እኔ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እኔ ብድ​ራ​ትን እከ​ፍ​ላ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ተብሎ ተጽ​ፎ​አ​ልና።

ሮሜ 12:11-19 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋት ወደ ኋላ አትበሉ። በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ። ችግረኛ ለሆኑ ቅዱሳን ካላችሁ አካፍሉ፤ እንግዶችን ተቀበሉ። የሚያሳድዷችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያዝኑም ጋራ ዕዘኑ። እርስ በርሳችሁ በአንድ ሐሳብ በመስማማት ኑሩ። ዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ካሉ ጋራ ዐብራችሁ ለመሆን ፍቀዱ እንጂ አትኵራሩ፤ በራሳችሁም አትመኩ። ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ትጉ። ቢቻላችሁስ በበኩላችሁ ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ኑሩ። ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቍጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ ጌታ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” እንዳለ ተጽፏልና።

ሮሜ 12:11-19 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤ በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤ ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ። የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ። እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ። ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ። ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ። ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።

ሮሜ 12:11-19 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሳትታክቱ የጋለ መንፈስን ተከትላችሁ ጌታን አገልግሉ። በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ጊዜ ታገሡ፤ ሁልጊዜ ጸልዩ። አማኞች ወንድሞችን በችግራቸው እርዱ፤ በእንግድነት የሚመጡትንም ተቀበሉ። የሚያሳድዱአችሁንም መርቁ፤ መርቁአቸው እንጂ አትርገሙአቸው። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ። እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ራሳችሁን ከፍ ከማድረግ ይልቅ ትዕቢትን አስወግዳችሁ ከድኾች ጋር በአንድነት ኑሩ፤ በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ። በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አድርጉ እንጂ፥ ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርጉባችሁ፥ እናንተም መልሳችሁ ክፉ ነገር አታድርጉባቸው። የሚቻላችሁ ቢሆን ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የሚያስፈልገውን ሁሉ አድርጉ። ወዳጆቼ ሆይ! ቊጣን ለእግዚአብሔር ተዉ እንጂ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ “የምበቀልና የበቀልንም ብድራት የምከፍል እኔ ነኝ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአል።

ሮሜ 12:11-19 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ጌታን አገልግሉ፤ በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤ ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ተቀበሉ። የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ። እርስ በርሳችሁ በአንድ ነገር ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፤ ነገር ግን የተናቁትን ቅረቡ። በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ። ለማንም በክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አስቡ። ቢቻላችሁ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ። “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ” ተብሎ ተጽፎአልና፥ ተወዳጆች ሆይ! ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ለቁጣው ቦታ ስጡ እንጂ።