ሮሜ 12:10-11
ሮሜ 12:10-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት መዋደድ ተዋደዱ፤ የምትራሩም ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ መምህሮቻችሁንም አክብሩ። ለሥራ ከመትጋት አትስነፉ፤ በመንፈስ ሕያዋን ሁኑ፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤
ያጋሩ
ሮሜ 12 ያንብቡሮሜ 12:10-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እርስ በርሳችሁ በወንድማማች መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ አንዱ ሌላውን ከራሱ በማስበለጥ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ። ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋት ወደ ኋላ አትበሉ።
ያጋሩ
ሮሜ 12 ያንብቡሮሜ 12:10-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤
ያጋሩ
ሮሜ 12 ያንብቡሮሜ 12:10-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ለመከባበርም ተሽቀዳደሙ፤ ሳትታክቱ የጋለ መንፈስን ተከትላችሁ ጌታን አገልግሉ።
ያጋሩ
ሮሜ 12 ያንብቡ