ሮሜ 10:16-17
ሮሜ 10:16-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነገር ግን ሁሉም የወንጌልን ትምህርት የሰሙ አይደለም፤ ኢሳይያስም፥ “አቤቱ፥ ምስክርነታችንንስ ማን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንዱ ለማን ተገለጠ?” ብሎአልና። ማመን ከመስማት ነው፤ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡሮሜ 10:16-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነገር ግን የሰሙት ሁሉ የምሥራቹን ቃል አልተቀበሉም፤ ኢሳይያስም፣ “ጌታ ሆይ፤ መልእክታችንን ማን አምኗል?” ብሏልና። እንግዲያስ እምነት የሚገኘው መልእክቱን ከመስማት ነው፤ መልእክቱም በክርስቶስ ቃል ነው።
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡሮሜ 10:16-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ነገር ግን ሁሉ ለምሥራቹ ቃል አልታዘዙም። ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ፥ ምስክርነታችንን ማን አመነ? ብሎአልና። እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡሮሜ 10:16-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ነገር ግን ኢሳይያስ፥ “ጌታ ሆይ! የተናገርነውን ቃል ማን ተቀበለ” ብሎ እንደ ተናገረ፥ ሁሉም የምሥራቹን ቃል አልተቀበሉም። ስለዚህ እምነት የሚገኘው የምሥራቹን ቃል ከመስማት ነው፤ የምሥራቹም ቃል የሚገኘው ስለ ክርስቶስ ከሚነገረው ትምህርት ነው።
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡ