ሮሜ 10:11-13
ሮሜ 10:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
መጽሐፍ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም” ይላልና። በአይሁዳዊና በግሪካዊ መካከል ልዩነት የለምና፤ ያው ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።”
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡሮሜ 10:11-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
መጽሐፍ፥ “የሚያምንበት ሁሉ አያፍርም” ብሎአል። አይሁዳዊንና አረማዊን አልለየም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ እግዚአብሔር ባለጸጋ ስለሆነ ለለመነው ሁሉ ይበቃልና። “የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡሮሜ 10:11-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
መጽሐፍ እንደሚለው፣ “በርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም።” በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ልዩነት የለም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፤ የሚለምኑትንም አብዝቶ ይባርካል፤ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡሮሜ 10:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና። በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡ