ሮሜ 1:22-23
ሮሜ 1:22-23 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“ጥበበኞች ነን” ሲሉ ሞኞች ሆኑ። የማያልፈውን እግዚአብሔርን በማክበር ፈንታ ኀላፊ በሆነው በሰው ምስል፥ በወፍ፥ አራት እግሮች ባሉአቸው እንስሶች፥ በመሬት ላይ በሚሳቡ እንስሶች መልክ ለተሠራው ምስል ክብርን ሰጡ።
ያጋሩ
ሮሜ 1 ያንብቡሮሜ 1:22-23 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ጥበበኞች ነን ሲሉ ሞኞች ሆኑ፤ የማይጠፋውን የእግዚአብሔርን ክብር በሚጠፋው በሰው፥ በወፎች፥ አራት እግር ባላቸው እንስሳትና በመሬት ላይ በሚሳቡ እንስሳት መልክ ምስል ለወጡ።
ያጋሩ
ሮሜ 1 ያንብቡሮሜ 1:22-23 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ጥበበኞች ነን ሲሉ አላዋቆች ሆኑ። የማይሞተውን የእግዚአብሔርን ክብር በሚሞት ሰውና በዎፎች፥ አራት እግር ባላቸውም፥ በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ።
ያጋሩ
ሮሜ 1 ያንብቡሮሜ 1:22-23 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ጥበበኞች ነን ቢሉም፣ ሞኞች ሆኑ፤ የዘላለም አምላክን ክብር ምዉት በሆነው ሰው፣ በወፎች፣ በእንስሳትና በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት መልክ መስለው ለወጡ።
ያጋሩ
ሮሜ 1 ያንብቡሮሜ 1:22-23 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ።
ያጋሩ
ሮሜ 1 ያንብቡ