ሮሜ 1:1-7

ሮሜ 1:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ወን​ጌል ለማ​ስ​ተ​ማር ተለ​ይቶ ከተ​ጠራ ሐዋ​ርያ፥ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋይ ከሚ​ሆን ከጳ​ው​ሎስ፥ በነ​ቢ​ያቱ ቃልና በቅ​ዱ​ሳት መጻ​ሕ​ፍት አስ​ቀ​ድሞ በተ​ስፋ ያና​ገ​ረው፥ ከዳ​ዊት ዘር ሰው ሆኖ በሥጋ ስለ ተወ​ለደ ስለ ልጁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ በኀ​ይ​ሉና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ በመ​ነ​ሣቱ ስለ አሳየ ስለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ፥ በስሙ እን​ዲ​ያ​ምኑ አሕ​ዛ​ብን ልና​ስ​ተ​ምር ሐዋ​ር​ያት ተብ​ለን የተ​ሾ​ም​ን​በ​ትና ጸጋን ያገ​ኘ​ን​በት፥ እና​ን​ተም ዛሬ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ለማ​መን እንደ ተጠ​ራ​ችሁ። በሮሜ ላላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ወ​ዳ​ችሁ፥ ለመ​ረ​ጣ​ች​ሁና ላከ​በ​ራ​ችሁ ሁሉ፥ ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።