መዝሙር 98:1-3 - Compare All Versions

መዝሙር 98:1-3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ፥ አሕ​ዛብ ደነ​ገጡ፤ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መጠ፥ ምድ​ርን አነ​ዋ​ወ​ጣት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ታላቅ ነው፤ እር​ሱም በአ​ሕ​ዛቡ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ። ሁሉ ታላቅ ስም​ህን ያመ​ሰ​ግ​ናል፥ ግሩ​ምና ቅዱስ ነውና።

መዝሙር 98:1-3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤ እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጓልና፤ ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም ማዳንን አድርገውለታል። እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤ ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ። ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣ ታማኝነቱንም ዐሰበ፤ የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣ የአምላካችንን ማዳን አዩ።

መዝሙር 98:1-3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ድንቅ ነገሮችን ስላደረገና፥ በኀያል ሥልጣኑ ድልን ስለ ተጐናጸፈ፥ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩለት! እግዚአብሔር አዳኝነቱ እንዲታወቅ አደረገ፤ ጽድቁንም ለአሕዛብ ገለጠ። ለእስራኤል ሕዝብ የሰጠውን ፍቅርና ታማኝነት አስታውሶአል፤ በየስፍራው ያሉ ሕዝቦች ሁሉ የአምላካችንን ድል አድራጊነት አይተዋል።

መዝሙር 98:1-3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ለጌታ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፥ ድንቅ ነገሮችን አድርጎአልና፥ ቀኙ፥ የተቀደሰ ክንዱም ለእርሱ ማዳን አደረገ። ጌታ ማዳኑን አስታወቀ፥ በአሕዛብም ፊት ጽድቁን ገለጠ። ለእስራኤል ቤት ያለውን ጽኑ ፍቅርና ታማኝነት አስታወሰ፥ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን አዩ።