መዝሙር 86:5-7 - Compare All Versions

መዝሙር 86:5-7 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ሰው እና​ታ​ችን ጽዮን ይላል፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ሰው ተወ​ለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠ​ረ​ታት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ለተ​ወ​ለ​ዱት አለ​ቆ​ችዋ በመ​ጽ​ሐፍ ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል። በአ​ንቺ የሚ​ኖሩ ሁሉ ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል።

መዝሙር 86:5-7 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ጌታ ሆይ፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ነህ፤ ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም። እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን አድምጥ፤ የልመናዬን ጩኸት ስማ። አንተ ስለምትመልስልኝ፣ በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ።

መዝሙር 86:5-7 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጌታ ሆይ! አንተ ለእኛ ቸርና መሐሪ ነህ፤ ወደ አንተ ለሚጸልዩትም ሁሉ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ታሳያቸዋለህ። እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ የልመናዬንም ጩኸት አድምጥ። አንተ ለጸሎቴ መልስ ስለምትሰጥ በመከራ ጊዜ ወደ አንተ እጮኻለሁ።

መዝሙር 86:5-7 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አቤቱ፥ አንተ መልካምና ይቅር ባይ ነህና፥ ጽኑ ፍቅርህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና። አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ የልመናዬንም ድምፅ ስማ። ትመልስልኛለህና በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጠራለሁ።