መዝሙር 6:5-7 - Compare All Versions

መዝሙር 6:5-7 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በሞት የሚ​ያ​ስ​ብህ የለ​ምና፥ በሲ​ኦ​ልም የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ንህ ማን ነው? በጭ​ን​ቀቴ ደክ​ሜ​አ​ለሁ፤ ሌሊ​ቱን ሁሉ አል​ጋ​ዬን አጥ​ባ​ለሁ፥ በዕ​ን​ባ​ዬም መኝ​ታ​ዬን አር​ሳ​ለሁ። ዐይኔ ከቍጣ የተ​ነሣ ታወ​ከች፤ ከጠ​ላ​ቶቼ ሁሉ የተ​ነሣ አረ​ጀሁ።

መዝሙር 6:5-7 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤ በሲኦልስ ማን ያመሰግንሃል? ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ። ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤ መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ። ዐይኖቼ በሐዘን ብዛት ደክመዋል፤ ከጠላቶቼም ሁሉ የተነሣ ማየት ተስኗቸዋል።

መዝሙር 6:5-7 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከሞቱት መካከል አንድም የሚያስታውስህ የለም። በመቃብርስ ሆኖ የሚያመሰግንህ ማነው? ከሐዘኔ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ከለቅሶዬ ብዛት የተነሣ በየሌሊቱ አልጋዬ በእንባ ይረጥባል፤ ትራሴም ይርሳል። ከጠላቶቼ ተቃውሞ የተነሣ በጣም በማልቀሴ ዐይኖቼ ፈዘዋል፤ ማየትም ተስኖኛል።

መዝሙር 6:5-7 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥ ስለ ቸርነትህም አድነኝ። በሞት የሚያስታውስህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው? በመቃተቴ ደክሜአለሁ፥ ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን በእንባ አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።