መዝሙር 53:1-3
መዝሙር 53:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥ በኀይልህም ፍረድልኝ። አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ የአፌንም ቃል አድምጥ፤ ባዕዳን በእኔ ላይ ቆመዋልና፥ ኀያላንም ነፍሴን ሽተዋታልና። እግዚአብሔርንም በፊታቸው አላደረጉትም።
ያጋሩ
መዝሙር 53 ያንብቡመዝሙር 53:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሞኝ በልቡ፣ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤ በጎ ነገር የሚሠራ አንድ እንኳን የለም። የሚያስተውል፣ እግዚአብሔርን የሚፈልግ እንዳለ ለማየት፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ። ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤ በአንድነትም ተበላሹ፤ መልካም የሚያደርግ የለም፤ አንድ እንኳ።
ያጋሩ
መዝሙር 53 ያንብቡመዝሙር 53:1-3 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ሞኞች በልባቸው “እግዚአብሔር የለም” ይላሉ፤ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች የተበላሹ ናቸው፤ አጸያፊ ድርጊቶችንም ይፈጽማሉ፤ ከእነርሱ መካከል መልካም ነገርን የሚያደርግ አንድም የለም። አስተዋዮችና እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሰዎች እንዳሉ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ። ነገር ግን ሁሉም ባዝነዋል፤ ሁሉም በአንድነት ተበላሽተዋል፤ ከእነርሱ አንድ እንኳ መልካም ነገርን የሚያደርግ የለም።
ያጋሩ
መዝሙር 53 ያንብቡ