መዝሙር 5:10-12
መዝሙር 5:10-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በነገረ ሠሪነታቸውም ይውደቁ፤ እንደ ሐሰታቸውም ብዛት አሳድዳቸው፥ አቤቱ፥ እነርሱ አሳዝነውሃልና። በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ ለዘለዓለሙ ደስ ይላቸዋል፥ በእነርሱም ታድራለህ። ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ። አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ አላባሽ ጋሻ ከለልኸን።
ያጋሩ
መዝሙር 5 ያንብቡመዝሙር 5:10-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አምላክ ሆይ፤ የእጃቸውን ስጣቸው! ተንኰላቸው መውደቂያቸው ይሁን፤ ከኀጢአታቸው ብዛት የተነሣ አስወግዳቸው፣ በአንተ ላይ ዐምፀዋልና። አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፤ ዘላለም በደስታ ይዘምሩ፤ ስምህን የሚወድዱ በአንተ ደስ እንዲላቸው፣ ተከላካይ ሁንላቸው። እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቃንን ትባርካቸዋለህ፤ በሞገስህም እንደ ጋሻ ትከልላቸዋለህ።
ያጋሩ
መዝሙር 5 ያንብቡመዝሙር 5:10-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አምላክ ሆይ! ፍረድባቸው፤ የራሳቸው ሤራ መውደቂያቸው ይሁን፤ በአንተ ላይ ስለ ዐመፁ ስለ ብዙ በደላቸው አስወግዳቸው፤ በአንተ ከለላ ሥር ያሉ ሁሉ ይደሰቱ፤ ለዘለዓለምም እልል ይበሉ የአንተን ስም የሚወዱትን ሁሉ በደስታም እንዲፈነድቁ ከልላቸው። እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ጻድቃንን ትባርካለህ፤ በቸርነትህም እንደ ጋሻ መከላከያ ትሆንላቸዋለህ።
ያጋሩ
መዝሙር 5 ያንብቡ