መዝሙር 48:10 - Compare All Versions

መዝሙር 48:10 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ጠቢ​ባ​ንን ሲሞቱ ባየ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ እን​ደ​ዚሁ ልብ የሌ​ላ​ቸው ሰነ​ፎች ይጠ​ፋሉ፥ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ው​ንም ለሌ​ሎች ይተ​ዋሉ።

መዝሙር 48:10 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤ ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት።

መዝሙር 48:10 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

አምላክ ሆይ! ምስጋናህ እስከ ዓለም ዳርቻ እንደ ደረሰ ስምህም እንደዚሁ ገናና ነው።

መዝሙር 48:10 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አምላክ ሆይ፥ በመቅደስህ ውሰጥ ርኅራኄህን አሰላሰልን።