መዝሙር 48:1-14

መዝሙር 48:1-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባዋል። የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው፣ በሰሜን በኩል በርቀት የሚታየው፣ በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ፣ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው። እግዚአብሔር በአዳራሾቿ ውስጥ ሆኖ፣ ብርቱ ምሽግ እንደ ሆናት አስመስክሯል። እነሆ፤ ነገሥታት ተባብረው መጡ፤ አንድ ላይ ሆነውም ገሠገሡ። አይተውም ተደነቁ፤ ደንግጠውም ፈረጠጡ። ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ በዚያ ብርክ ያዛቸው። የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር፣ አንተ አብረከረክሃቸው። እንደ ሰማን፣ በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ከተማ፣ በአምላካችን ከተማ፣ እንዲሁ አየን፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል። ሴላ አምላክ ሆይ፤ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን፣ ምሕረትህን እናስባለን። አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤ ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት። ስለ ፍርድህ፣ የጽዮን ተራራ ሐሤት ታድርግ፤ የይሁዳ መንደሮችም ደስ ይበላቸው። በጽዮን አካባቢ ተመላለሱ፤ ዙሪያዋንም ሂዱ፤ የጥበቃ ግንቦቿንም ቍጠሩ፤ ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ፣ መከላከያ ዕርዶቿን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ መጠበቂያ ማማዎቿን እዩ። ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነውና፤ እስከ መጨረሻው የሚመራንም እርሱ ነው።

መዝሙር 48:1-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ ይህን ስሙ፤ በዓ​ለም የም​ት​ኖ​ሩም ሁላ​ችሁ፥ አድ​ምጡ፤ የሰው ልጆች ባለ​ጠ​ጎ​ችና ድሆች፥ በየ​ሀ​ገ​ራ​ችሁ በአ​ን​ድ​ነት። አፌ ጥበ​ብን ይና​ገ​ራል፥ የል​ቤም ዐሳብ ምክ​ርን፥ በጆ​ሮዬ ምሳሌ አደ​ም​ጣ​ለሁ፥ በበ​ገ​ናም ነገ​ሬን እገ​ል​ጣ​ለሁ። ከክፉ ቀን ለምን እፈ​ራ​ለሁ? ኀጢ​አት ተረ​ከ​ዜን ከበ​በኝ፤ በኀ​ይ​ላ​ቸው የሚ​ታ​መኑ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ታ​ቸ​ውም ብዛት የሚ​ኮሩ፤ ወን​ድም ወን​ድ​ሙን አያ​ድ​ንም፥ ሰውም አያ​ድ​ንም፤ ቤዛ​ው​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ሰ​ጥም፥ የነ​ፍ​ሱ​ንም ዋጋ ለውጥ፥ በዓ​ለም የደ​ከመ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይድ​ናል፥ ጥፋ​ትን አያ​ይ​ምና። ጠቢ​ባ​ንን ሲሞቱ ባየ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ እን​ደ​ዚሁ ልብ የሌ​ላ​ቸው ሰነ​ፎች ይጠ​ፋሉ፥ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ው​ንም ለሌ​ሎች ይተ​ዋሉ። መቃ​ብ​ራ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቤታ​ቸው ነው፥ ማደ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ለልጅ ልጅ ነው፤ በየ​ሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም ስማ​ቸው ይጠ​ራል። ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አላ​ወ​ቀም፤ ልብ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው እን​ስ​ሶ​ችም ሆነ፥ መሰ​ላ​ቸ​ውም። በአ​ፋ​ቸው ሲወዱ፥ ራስዋ መን​ገ​ዳ​ቸው መሰ​ና​ክ​ላ​ቸው ናት፥ እንደ በጎች ሞት በሲ​ኦል ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ቅኖ​ችም በማ​ለዳ ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፥ ረድ​ኤ​ታ​ቸ​ውም ከክ​ብ​ራ​ቸው ተለ​ይታ በሲ​ኦል ትጠ​ፋ​ለች።

መዝሙር 48:1-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባዋል። የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው፣ በሰሜን በኩል በርቀት የሚታየው፣ በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ፣ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው። እግዚአብሔር በአዳራሾቿ ውስጥ ሆኖ፣ ብርቱ ምሽግ እንደ ሆናት አስመስክሯል። እነሆ፤ ነገሥታት ተባብረው መጡ፤ አንድ ላይ ሆነውም ገሠገሡ። አይተውም ተደነቁ፤ ደንግጠውም ፈረጠጡ። ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ በዚያ ብርክ ያዛቸው። የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር፣ አንተ አብረከረክሃቸው። እንደ ሰማን፣ በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ከተማ፣ በአምላካችን ከተማ፣ እንዲሁ አየን፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል። ሴላ አምላክ ሆይ፤ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን፣ ምሕረትህን እናስባለን። አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤ ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት። ስለ ፍርድህ፣ የጽዮን ተራራ ሐሤት ታድርግ፤ የይሁዳ መንደሮችም ደስ ይበላቸው። በጽዮን አካባቢ ተመላለሱ፤ ዙሪያዋንም ሂዱ፤ የጥበቃ ግንቦቿንም ቍጠሩ፤ ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ፣ መከላከያ ዕርዶቿን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ መጠበቂያ ማማዎቿን እዩ። ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነውና፤ እስከ መጨረሻው የሚመራንም እርሱ ነው።

መዝሙር 48:1-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ታላቅ ስለ ሆነ በአምላካችን ከተማ፤ በተቀደሰ ተራራው ላይ ከፍ ያለ ምስጋና ሊቀርብለት ይገባዋል። በሰሜን በኩል የምትገኘው፥ በከፍታዋና በውበትዋ የምትደነቀው፥ የጽዮን ተራራ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች፤ እርስዋም በምድር ላሉ ሁሉ ደስታን ታጐናጽፋለች። እግዚአብሔር በምሽግዋ ውስጥ ነው፤ እርሱም ከለላዋ መሆኑን አስመስክሮአል። ከተማይቱን ለማጥቃት ነገሥታት ኀይላቸውን አሰባሰቡ። ነገር ግን ባዩአት ጊዜ ደነገጡ፤ ፈርተውም ሸሹ። እዚያም ሳሉ በፍርሃት ተርበደበዱ፤ ምጥ እንደ ያዛትም ሴት ተጨነቁ። በምሥራቅ ነፋስ እንደሚሰባበሩ የተርሴስ መርከቦች ሆኑ። እግዚአብሔር ያደረገውን ሰምተናል፤ አሁንም ሁሉን ቻይ ጌታ የራሱ በሆነችው ከተማ ያደረገውን በዐይናችን አየን፤ እርሱ ከተማይቱን ለዘለዓለም ጸንታ እንድትኖር ያደርጋታል። አምላክ ሆይ! በመቅደስህ ውስጥ ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እናስባለን። አምላክ ሆይ! ምስጋናህ እስከ ዓለም ዳርቻ እንደ ደረሰ ስምህም እንደዚሁ ገናና ነው። ፍርድህ ትክክለኛ ስለ ሆነ በጽዮን የሚኖሩ ሕዝቦች ደስ ይላቸዋል፤ በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ሐሴት ያደርጋሉ። ተሰልፋችሁ ጽዮንን ዙሩአት፤ ማማዎችዋንም ቊጠሩ። ለሚመጣው ትውልድ ታስተላልፉ ዘንድ ጠንካራ ቅጥሮችዋን አስተውሉ፤ ምሽጎችዋንም ተመልከቱ። የምትነግሩአቸውም “እግዚአብሔር እንዲህ ነው፤ አምላካችን ዘለዓለማዊ ነው፤ ወደፊትም ለዘለዓለም ይመራናል” ብላችሁ ነው።

መዝሙር 48:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታ ትልቅ ነው፥ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው። በሰሜን በኩል በመልካም ስፍራ የቆመ የምድር ሁሉ ደስታ የጽዮን ተራራ ነው፥ እርሷም የትልቁ ንጉሥ ከተማ ነች። እግዚአብሔር በአዳራሾችዋ መጠጊያ ሆኖ ይታወቃል። እነሆ፥ ነገሥታት ተከማችተው በአንድነት መጥተዋል። እነርሱስ አይተው ተደነቁ፥ ደነገጡ፥ ሸሹም። በዚያ እንደ ወላድ ምጥ መንቀጥቀጥ ያዛቸው። በኃይለኛ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትሰብራለህ። እንደ ሰማን እንዲሁ አየን በሠራዊት ጌታ ከተማ፥ በአምላካችን ከተማ፥ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያጸናታል። አምላክ ሆይ፥ በመቅደስህ ውሰጥ ርኅራኄህን አሰላሰልን። አምላክ ሆይ፥ እንደ ስምህ ምስጋናህም እንዲሁ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ነው፥ ቀኝህ ጽድቅን የተሞላች ናት። አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ። ጽዮንን ክበቡአት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦችዋንም ቁጠሩ፥ በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥ ቅጥሮችዋን መርምሩ፥ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።