መዝሙር 41:7-10
መዝሙር 41:7-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራዋለች፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ። እግዚአብሔር በቀን ይቅርታውን ያዝዛል፥ በሌሊትም እርሱን ይናገራል፤ ከእኔ ዘንድ የሕይወቴ ብፅዐት ለእግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ አምላኬ ነህ፤ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን ተውኸኝ? ለምንስ አዝኜ እመለሳለሁ?” ጠላቶቼ ሁሉ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ። ሁልጊዜ፥ “አምላክህ ወዴት ነው?” ይሉኛልና።
ያጋሩ
መዝሙር 41 ያንብቡመዝሙር 41:7-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ጠላቶቼ ሁሉ ግንባር ፈጥረው ይንሾካሾኩብኛል፤ እንዲህ እያሉም፣ የከፋ ነገር በላዬ ያውጠነጥናሉ፤ “ምናምንቴ ነገር ይዞታል፤ ከእንግዲህም ከተኛበት አይነሣም።” እንጀራዬን የበላ፣ የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣ ተረከዙን አነሣብኝ። እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ምሕረት አድርግልኝ፤ የእጃቸውን እንድከፍላቸው አስነሣኝ።
ያጋሩ
መዝሙር 41 ያንብቡ