መዝሙር 4:6-8
መዝሙር 4:6-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“በጎውን ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች ናቸው። አቤቱ፥ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ። በልባችን ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን፥ ከዘይትም ይልቅ በዛ። በእርሱ በሰላም እተኛለሁ፥ አንቀላፋለሁም፤ አቤቱ፥አንተ ብቻህን በተስፋ አሳድረኸኛልና።
ያጋሩ
መዝሙር 4 ያንብቡመዝሙር 4:6-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል?” ይላሉ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ። ስንዴና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ባመረቱ ጊዜ ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ፣ አንተ ልቤን በታላቅ ሐሤት ሞልተኸዋል። በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ሥጋት የምታሳድረኝ አንተ ብቻ ነህና።
ያጋሩ
መዝሙር 4 ያንብቡ