መዝሙር 36:1-4
መዝሙር 36:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በክፉዎች ላይ አትቅና፥ ዐመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፤ እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፥ እንደ ለመለመ ቅጠልም ፈጥነው ይረግፋሉና። በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ያሳድርሃል፥ በሀብትዋም ያሰማርሃል። በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
ያጋሩ
መዝሙር 36 ያንብቡመዝሙር 36:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ክፉውን ሰው፣ በደል በልቡ ታናግረዋለች፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር፣ በዐይኖቹ ፊት የለም። በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ፣ ራሱን በራሱ እጅግ ይሸነግላልና። ከአንደበቱ የሚወጣው የክፋትና የተንኰል ቃል ነው፤ ማስተዋልንና በጎ ማድረግን ትቷል። በመኝታው ላይ ክፋትን ያውጠነጥናል፤ ራሱን በጎ ባልሆነ መንገድ ይመራል፤ ክፋትንም አያርቅም።
ያጋሩ
መዝሙር 36 ያንብቡ