መዝሙር 36:1-12

መዝሙር 36:1-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በክ​ፉ​ዎች ላይ አት​ቅና፥ ዐመ​ፃ​ንም በሚ​ያ​ደ​ርጉ ላይ አት​ቅና፤ እንደ ሣር ፈጥ​ነው ይደ​ር​ቃ​ሉና፥ እንደ ለመ​ለመ ቅጠ​ልም ፈጥ​ነው ይረ​ግ​ፋ​ሉና። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመን፥ መል​ካ​ም​ንም አድ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ያሳ​ድ​ር​ሃል፥ በሀ​ብ​ት​ዋም ያሰ​ማ​ር​ሃል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ልህ፥ የል​ብ​ህ​ንም መሻት ይሰ​ጥ​ሃል። መን​ገ​ድ​ህን ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጥ፥ በእ​ር​ሱም ታመን፥ እር​ሱም ያደ​ር​ግ​ል​ሃል። ጽድ​ቅ​ህን እንደ ብር​ሃን፥ ፍር​ድ​ህ​ንም እንደ ቀትር ያመ​ጣ​ታል። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዛ አገ​ል​ግ​ለ​ውም። በሕ​ይ​ወቱ ደስ ባለ​ውና ዐመ​ፃን በሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው ላይ አት​ቅና። መዓ​ትን ተዋት፤ ቍጣ​ንም ጣላት፥ እን​ዳ​ት​በ​ድ​ልም አት​ቅና። ክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎች ይጠ​ፋ​ሉና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ግን እነ​ርሱ ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ። ኀጢ​አ​ተ​ኛም ገና ጥቂት አይ​ኖ​ርም፤ ትፈ​ል​ገ​ዋ​ለህ፥ ቦታ​ው​ንም አታ​ገ​ኝም። የዋ​ሆች ግን ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ፥ በብ​ዙም ሰላም ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ኀጢ​አ​ተኛ ጻድ​ቁን ይመ​ለ​ካ​ከ​ተ​ዋል፥ ጥር​ሱ​ንም በእ​ርሱ ላይ ያፋ​ጫል።

መዝሙር 36:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ክፉውን ሰው፣ በደል በልቡ ታናግረዋለች፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር፣ በዐይኖቹ ፊት የለም። በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ፣ ራሱን በራሱ እጅግ ይሸነግላልና። ከአንደበቱ የሚወጣው የክፋትና የተንኰል ቃል ነው፤ ማስተዋልንና በጎ ማድረግን ትቷል። በመኝታው ላይ ክፋትን ያውጠነጥናል፤ ራሱን በጎ ባልሆነ መንገድ ይመራል፤ ክፋትንም አያርቅም። እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤ ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ይመጥቃል። ጽድቅህ እንደ ታላላቅ ተራሮች፣ ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰውንም እንስሳንም ታድናለህ። አምላክ ሆይ፤ ምሕረትህ እንዴት ክቡር ነው! የሰዎች ልጆች ሁሉ፣ በክንፎችህ ጥላ ሥር መጠጊያ ያገኛሉ። ከቤትህ ሲሳይ ይመገባሉ፤ ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ። የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፣ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን። ለሚያውቁህ ምሕረትህ፣ ልባቸውም ለቀና ጽድቅህ ዘወትር አይቋረጥባቸው። የትዕቢተኛ እግር በላዬ አይምጣ፤ የክፉውም ሰው እጅ አያሳድደኝ። ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁና እንደ ተጋደሙ፣ ቍልቍልም እንደ ተወረወሩና መነሣት እንደማይችሉ ተመልከት!

መዝሙር 36:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ክፉ ሰው ሁልጊዜ በልቡ ክፋትን ያስባል፤ እግዚአብሔርን ከቶ አይፈራም፤ አያከብረውምም። ክፉ ሰው ክፋቱ ስለሚያቈላምጠው ኃጢአቱን ለማየትም ሆነ ለመጥላት አይፈልግም። ንግግሩ ተንኰልንና ሐሰትን የተሞላ ነው፤ መልካም ሥነ ምግባርን ሁሉ መረዳት አቃተው። በመኝታውም ላይ ሳለ ተንኰልን ያቅዳል፤ ራሱን ወደ ክፉ መንገድ ይመራል። ክፉውን ነገር አያስወግድም። እግዚአብሔር ሆይ፥ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ እስከ ሰማይ፥ እውነተኛነትህም እስከ ደመና ይደርሳል። እግዚአብሔር ሆይ፥ ሰዎችንና እንስሶችን ከአደጋ ታድናለህ፤ ጽድቅህ እንደ ተራራዎች እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ፍርድህም እንደ ባሕር ጥልቅ ነው። አምላክ ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው! ሰዎች በአንተ ጥበቃ ሥር ይከለላሉ። በቤትህ የተትረፈረፈውን ምግብ ይጋበዛሉ፤ አስደሳች ከሆነ ወንዝህም ታጠጣቸዋለህ። አንተ የሕይወት ሁሉ ምንጭ ነህ፤ ከአንተም ብርሃን የተነሣ ብርሃን እናያለን፤ ለሚያውቁህ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ አይቋረጥባቸው፤ አዳኝነትህም ለልበ ቅኖች ይቀጥል። የትዕቢተኞች እግር እንዲረግጠኝ፥ የክፉዎች እጅ እንዲአባርረኝ አታድርግ። ክፉዎች እንዴት እንደ ወደቁ እይ። እነሆ ተጥለዋል፤ መነሣትም አይችሉም።