መዝሙር 21:8-13 - Compare All Versions
መዝሙር 21:8-13 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፤ ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ፈልጋ ትይዛለች። በምትገለጥበት ጊዜ፣ እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ፤ እግዚአብሔር በመዓቱ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል፤ እሳቱም ሙጥጥ አድርጋ ትበላቸዋለች። ዘራቸውን ከምድር፣ ዘር ማንዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ። ክፋት ቢያስቡብህ፣ ተንኰል ቢወጥኑብህም አይሳካላቸውም፤ በመጡበት ትመልሳቸዋለህና፤ ቀስትህንም በፊታቸው ላይ ታነጣጥራለህ። እግዚአብሔር ሆይ፤ በብርታትህ ከፍ ከፍ በል፤ ኀይልህን እናወድሳለን፤ እንዘምራለንም።
መዝሙር 21:8-13 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ፥ ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ሁሉ ያገኛል። በምትገለጥበት ጊዜ ከምድጃ እንደሚወጣ የእሳት ነበልባል ታቃጥላቸዋለህ፤ እግዚአብሔር በቊጣው ወላፈን ይለበልባቸዋል፤ እሳትም ይበላቸዋል። ትውልዳቸውን ከምድር ላይ ታጠፋለህ፤ ዘራቸውንም ከሕዝቦች መካከል ለይተህ ትደመስሳለህ። በአንተ ላይ ክፉ ነገር ለማድረግ ቢያቅዱና ቢያድሙም ምንም አይሳካላቸውም። ፍላጻዎችህን በእነርሱ ላይ ታነጣጥራለህ፤ ወደ ኋላም ተመልሰው እንዲሸሹ ታደርጋለህ። እግዚአብሔር ሆይ! ልዕልናህ ከፍ ከፍ ይበል፤ ስለ ታላቁ ኀይልህም የምስጋና መዝሙር እናቀርባለን።
መዝሙር 21:8-13 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
“በእግዚአብሔር አመነ፥ እርሱንም ያድነው፤ ከወደደው ያድነው።” አንተ ከሆድ አውጥተኸኛልና፥ በእናቴ ጡት ሳለሁም በአንተ ታመንሁ። ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልሁ፤ ከእናቴ ማኅፀን ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ። ልጨነቅ ቀርቤአለሁና፥ የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ። ብዙ በሬዎች ከበቡኝ፥ የሰቡትም ፍሪዳዎች ያዙኝ፤ ለመንጠቅ እንደሚያሸምቅ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ።
መዝሙር 21:8-13 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ንጉሥ በጌታ ተማምኖአልና፥ በልዑልም ጽኑ ፍቅር አይናወጥም። እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፥ ቀኝህም የሚጠሉህን ሁሉ ታገኛቸዋለች። በተቈጣህም ጊዜ እንደ እሳት እቶን ታደርጋቸዋለህ፥ ጌታ በቁጣው ይውጣቸዋል፥ እሳትም ትበላቸዋለች። ፍሬአቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ። ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥ የማይቻላቸውንም ምክር አሰቡ። ወደ ኋላቸው ትመልሳቸዋለህ፥ ፍላጻን በፊታቸው ላይ ታዘጋጃለህ።