መዝሙር 18:32-35
መዝሙር 18:32-35 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቀና እርሱ እግዚአብሔር ነው። እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል። እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤ ክንዶቼም የናስ ቀስት መገተር ይችላሉ። የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች፤ ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል።
ያጋሩ
መዝሙር 18 ያንብቡ