መዝሙር 18:18-19 - Compare All Versions

መዝሙር 18:18-19 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እነርሱ በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ድጋፍ ሆነኝ። ወደ ሰፊ ስፍራ አወጣኝ፤ ደስ ተሰኝቶብኛልና አዳነኝ።

መዝሙር 18:18-19 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እኔ በተቸገርኩበት ጊዜ በጠላትነት ተነሡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ጠበቀኝ። ወደ ሰፊ ቦታ አወጣኝ፤ በእኔ ደስ ስለ ተሰኘም አዳነኝ።

መዝሙር 18:18-19 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከብርቱዎች ጠላቶቼ ከሚጠሉኝም አዳነኝ፥ በርትተውብኝ ነበርና። በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፥ ጌታ ግን ድጋፍ ሆነኝ።