መዝሙር 149:4-5 - Compare All Versions

መዝሙር 149:4-5 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ደስ ብሎ​ታ​ልና፥ የዋ​ሃ​ን​ንም በማ​ዳኑ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋ​ልና። ጻድ​ቃን በክ​ብሩ ይመ​ካሉ፤ በመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ላይ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ።

መዝሙር 149:4-5 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤ የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል። ቅዱሳን በዚህ ክብር ይጓደዱ፤ በመኝታቸውም ላይ እልል እያሉ ይዘምሩ።

መዝሙር 149:4-5 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋል፤ ድል በማቀዳጀት ትሑታንን ያከብራቸዋል። የእግዚአብሔር ሕዝቦች በድል አድራጊነታቸው ደስ ይበላቸው፤ ሌሊቱን በሙሉ በደስታ ይዘምሩ።

መዝሙር 149:4-5 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ጌታ በሕዝቡ ተደስቶአልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ያስጌጣቸዋል። ቅዱሳን በክብር ይመካሉ፥ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ።