መዝሙር 146:1-7
መዝሙር 146:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና። ለአምላካችንም ምስጋና ማቅረብ ያማረ ነው። እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይሠራታል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል። ልባቸው የቈሰለውን ይፈውሳል፥ ቍስላቸውንም ያደርቅላቸዋል። ከዋክብትንም በሙሉ ይቈጥራቸዋል፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል። እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ ኀይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር የለውም። እግዚአብሔር የዋሃንን ያነሣቸዋል፥ ኃጥአንን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳቸዋል። ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፤
መዝሙር 146:1-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ። በምኖርበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ። በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችም አትመኩ። መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤ ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር ይሆናል። ብፁዕ ነው፤ ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣ ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው፤ እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ፣ ታማኝነቱም ለዘላለም የሆነ ነው፤ ለተበደሉት የሚፈርድ፣ ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤
መዝሙር 146:1-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ይመስገን! ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! በሕይወቴ ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ። ማዳን ስለማይችሉ በመሪዎች ወይም በማንኛውም ፍጡር አትተማመኑ። እነርሱ በሚሞቱበት ጊዜ ወደ ዐፈር ይመለሳሉ፤ በዚያኑ ቀን ዕቅዳቸው ሁሉ ይጠፋል። የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነለትና በአምላኩ በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረገ ሰው ደስ ይበለው፤ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ የፈጠረ ነው። እርሱ ዘወትር ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል፤ ለተጨቈኑት ፍትሕን ይሰጣል፤ ለተራቡ ምግብን ይሰጣል።
መዝሙር 146:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን አመስግኚ። በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ጌታን አመሰግናለሁ፥ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ። ማዳን በማይችሉ በአለቆች፥ በሰው ልጅ፥ አትታመኑ። ነፍሱ ትወጣለች ወደ መሬቱም ይመለሳል፥ ያንጊዜ እቅዶቹ በሙሉ ይጠፋሉ። የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በጌታ በአምላኩ የሆነ ሰው ምስጉን ነው፥ እርሱም ሰማይንና ምድርን ባሕርንም፥ በእነርሱ ያለውንም ሁሉ የፈጠረ፥ እውነትን ለዘለዓለም የሚጠብቅ፥ ለተበደሉት የሚፈርድ፥ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ ነው። ጌታ የታሰሩትን ይፈታል፥