መዝሙር 144:1-15

መዝሙር 144:1-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አም​ላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፥ ስም​ህ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ። በየ​ቀኑ ሁሉ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ ለስ​ም​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም ምስ​ጋና አቀ​ር​ባ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፥ ምስ​ጋ​ና​ውም እጅግ ብዙ ነው፤ ለታ​ላ​ቅ​ነ​ቱም ዳርቻ የለ​ውም። የልጅ ልጆች ሥራ​ህን ያደ​ን​ቃሉ፥ ኀይ​ል​ህ​ንም ይና​ገ​ራሉ፥ የቅ​ድ​ስ​ና​ህ​ንም ክብር ታላ​ቅ​ነት ይና​ገ​ራሉ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም ያስ​ረ​ዳሉ። “ኀይ​ልህ ግሩም ነው” ይላሉ፥ ግር​ማ​ህ​ንም ይነ​ጋ​ገ​ራሉ፥ ብር​ታ​ት​ህ​ንም ያስ​ረ​ዳሉ። የቸ​ር​ነ​ት​ህን ብዛት መታ​ሰ​ቢያ ይና​ገ​ራሉ፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ባይና መሓሪ ነው፥ መዐቱ የራቀ፥ ምሕ​ረቱ የበዛ እው​ነ​ተኛ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ታ​ገ​ሡት ቸር ነው። ይቅ​ር​ታ​ውም በሥ​ራው ሁሉ ላይ ነው። አቤቱ፥ ፍጥ​ረ​ትህ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፥ ጻድ​ቃ​ን​ህም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል። “ለመ​ን​ግ​ሥ​ትህ ክብር ይገ​ባል” ይላሉ፥ ኀይ​ል​ህ​ንም ይነ​ጋ​ገ​ራሉ፥ ለሰው ልጆች ኀይ​ል​ህን የመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህ​ንም ክብር ታላ​ቅ​ነት ያስ​ታ​ውቁ ዘንድ። መን​ግ​ሥ​ትህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሁሉ መን​ግ​ሥት ናት፥ ግዛ​ት​ህም ለልጅ ልጅ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃሉ ሁሉ የታ​መነ ነው፥ በሥ​ራ​ውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ሙ​ትን ሁሉ ይደ​ግ​ፋ​ቸ​ዋል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ቁ​ትን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል። የሰው ሁሉ ዐይን አን​ተን ተስፋ ያደ​ር​ጋል፤ አን​ተም ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።

መዝሙር 144:1-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እጆቼን ለጦርነት፣ ጣቶቼን ለውጊያ የሚያሠለጥን፣ እግዚአብሔር ዐለቴ ይባረክ። እርሱ አፍቃሪ አምላኬና ጽኑ ዐምባዬ ነው፤ ምሽጌና ታዳጊዬ፣ የምከለልበትም ጋሻዬ ነው፤ ሕዝቤን የሚያስገዛልኝም እርሱ ነው። እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ያህል በልብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ታስበውስ ዘንድ የሰው ልጅ እስከዚህ ምንድን ነው? ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤ ዘመኑም ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው። እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያትህን ሰንጥቀህ ውረድ፤ ይጤሱም ዘንድ ተራሮችን ዳስስ። የመብረቅ ብልጭታ ልከህ በትናቸው፤ ፍላጻህን ሰድደህ ግራ አጋባቸው። እጅህን ከላይ ዘርጋ፤ ከኀይለኛ ውሃ፣ ከባዕዳንም እጅ ታደገኝ፤ አድነኝም። አንደበታቸው ሐሰትን ይናገራል፤ ቀኝ እጃቸውም የቅጥፈት ቀኝ እጅ ናት። አምላክ ሆይ፤ አዲስ ቅኔ እቀኝልሃለሁ፤ ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ። ነገሥታትን ድል የሚያጐናጽፍ፣ ባሪያውን ዳዊትን ከሚጐዳ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው። አንደበታቸው ሐሰትን ከሚናገር፣ ቀኝ እጃቸው የቅጥፈት ቀኝ እጅ ከሆነችው፣ ከባዕዳን እጅ ታደገኝ፤ አድነኝም። ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው፣ የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል፣ ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ። ጐተራዎቻችን በተለያየ የእህል ዐይነት፣ የተሞሉ ይሁኑ፤ በጎቻችን እስከ ሺሕ ይውለዱ፤ በመስኮቻችንም እስከ ዐሥር ሺሕ ይባዙ። ከብቶቻችን ይክበዱ፤ አይጨንግፉ፤ አይጥፉም። እኛም በምርኮ አንወሰድ፤ በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይሰማ። ብፁዕ ነው፤ ይህ ባርኮት ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ፤ ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ።

መዝሙር 144:1-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

መጠጊያዬ እግዚአብሔር ይመስገን! ለሰልፍ ያሠለጥነኛል፤ ለጦርነትም ያዘጋጀኛል። እግዚአብሔር ጠባቂዬና መከታዬ ነው፤ መጠለያዬና አዳኜ ነው፤ በእርሱ ተማምኜ በሰላም እኖራለሁ፤ እርሱ አሕዛብን ከእግሬ በታች አድርጎ ያስገዛልኛል። እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ያኽል የምትንከባከበው ሰው ምንድን ነው? ይህን ያኽልስ የምታስብለት የሰው ልጅ ምንድን ነው? ሰው እንደ ነፋስ ሽውታ ነው፤ ዘመኑም እንደ ጥላ የሚያልፍ ነው። እግዚአብሔር ሆይ! ሰማይን ሰንጥቀህ ውረድ፤ ተራራዎችን ዳስስ፤ እነርሱም ይጢሱ። የመብረቅ ብልጭታን ልከህ ጠላቶችህን በትናቸው፤ ፍላጻዎችህንም በመወርወር አሳዳቸው። እጅህን ከላይ ስደድ፤ ከጥልቅ ውሃ ውስጥ ስበህ አውጣኝ፤ ታደገኝም፤ ከባዕዳን ኀይል አድነኝ። እነርሱ ከቶ እውነት አይናገሩም፤ ቀኝ እጃቸውን አንሥተው የሚምሉት በሐሰት ነው። አምላክ ሆይ! አዲስ መዝሙር እቀኝልሃለሁ፤ ዐሥር አውታር ያለው በገናም በመደርደር እዘምርልሃለሁ። አንተ ለነገሥታት ድልን ታጐናጽፋለህ፤ አገልጋይህን ዳዊትንም ከስለታም ሰይፍ ትታደገዋለህ። ከባዕዳን ጠላቶች እጅ ታድገህ አድነኝ፤ አፋቸው ሐሰትን ይናገራል፤ ቀኝ እጃቸውም ለሐሰት መሐላ ይነሣል። ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው ጊዜ እንደ አዲስ ተክል የሚያድጉና የሚጠነክሩ ይሁኑ፤ ሴቶች ልጆቻችን ለቤተ መንግሥት ማእዘኖች ውበት እንደሚሰጡ፥ ተቀርጸው ቀጥ እንዳሉ ምሰሶች ይሁኑ። ጐተራዎቻችን በልዩ ልዩ ዐይነት እህል የተሞሉ ይሁኑ፤ በመስኮቻችን ላይ የተሰማሩት በጎች በሺህ የሚቈጠሩ ግልገሎችን እየወለዱ ይብዙ። ከብቶቻችን የሰቡ ይሁኑ፤ ሳይጨነግፉም በመርባት ይብዙ፤ በመንገዶቻችን የሐዘን ጩኸት ከቶ አይሰማ። እንደዚህ የሚሆንለት ሕዝብ የተባረከ ነው! እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለት ሕዝብ የተባረከ ነው!

መዝሙር 144:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታዬ ዐለቴ፥ ይባረክ፥ ለእጆቼ ሰልፍን፥ ለጣቶቼም ዘመቻን የሚያስተምር፥ መሓሪዬና መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና መድኃኒቴ፥ ረዳቴና መታመኛዬም፥ ሕዝቤንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ። አቤቱ፥ እርሱን ታውቀው ዘንድ ሰው ምንድነው? ታስብለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው? ሰው ከንቱን ነገር ይመስላል፥ ዘመኑ እንደ ጥላ ያልፋል። አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው ውረድም፥ ተራሮችን ዳስሳቸው ይጢሱም። መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው በትናቸውም፥ ፍላጾችህን ላካቸው አስደንግጣቸውም። እጅህን ከአርያም ላክ አድነኝም ከብዙ ውኆች፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥ ቀኛቸው የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ። አቤቱ፥ አዲስ ቅኔ እቀኛልሃለሁ፥ ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ። ለነገሥታት መድኃኒትን የሚሰጥ፥ ባርያውን ዳዊትን ከክፉ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው። አድነኝ፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥ ቀኛቸውም የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ። ልጆቻቸን በጉልማስነታቸው እንደ አዲስ አትክልት ይሁኑ፥ ሴቶች ልጆቻቸንም እንደ እልፍኝ ይመሩና ያጊጡ፥ ዕቃ ቤቶቻቸንም ይሞሉ፥ በየዓይነቱም ዕቃ ይኑራቸው፥ በጎቻቸንም ብዙ ይውለዱ፥ በማሰማርያችንም ይብዙ፥ ላሞቻቸንም የሰቡ ይሁኑ፥ ቅጥራቸውም መፍረሻና መውጫ አይኑረው፥ በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይኑር፥ እንደዚህ የሚሆንለት ሕዝብ የተመሰገነ ነው፥ ጌታ አምላኩ የሆነለት ሕዝብ ምስጉን ነው።