መዝሙር 142:2-3
መዝሙር 142:2-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሕያው ሁሉ በፊትህ አይጸድቅምና ከባሪያህ ጋር ወደ ክርክር አትግባ። ጠላት ነፍሴን ከብቦአታልና ሕይወቴንም በምድር ውስጥ አዋርዶአታል፥ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኖሩኝ።
መዝሙር 142:2-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ፤ ችግሬንም በፊቱ እናገራለሁ። መንፈሴ በውስጤ ሲዝል፣ መንገዴን የምታውቅ አንተ ነህ፤ በመተላለፊያ መንገዴ ላይ፣ ወጥመድ በስውር ዘርግተውብኛል።