መዝሙር 134:1-3
መዝሙር 134:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ፤ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት። በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ፥ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ። እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ለስሙ ዘምሩ፥ መልካም ነውና፤
መዝሙር 134:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እናንተ በሌሊት ቆማችሁ በእግዚአብሔር ቤት የምታገለግሉ፣ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ እግዚአብሔርን ባርኩ። በመቅደሱ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፤ እግዚአብሔርንም ባርኩ። ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር፣ ከጽዮን ይባርክህ።