መዝሙር 133:1-3
መዝሙር 133:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በእግዚአብሔር ቤት፥ በአምላካችን ቤት አደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ። በሌሊት በቤተ መቅደስ እጆቻችሁን አንሡ፥ እግዚአብሔርንም አመስግኑት። ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ።
መዝሙር 133:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል! በራስ ላይ ፈስሶ፣ እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣ እስከ አሮን ጢም እንደሚወርድ፣ እስከ ልብሱም ዐንገትጌ እንደሚደርስ ውድ ሽቱ ነው። ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ፣ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን፣ ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዟልና።