መዝሙር 128:1-6
መዝሙር 128:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እስራኤል እንዲህ ይበል፥ “ከትንሽነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ተሰለፉብኝ፤ ከትንሽነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ተሰለፉብኝ፤ ነገር ግን አልቻሉኝም። ኃጥኣን በጀርባዬ ላይ መቱኝ፥ ኀጢአታቸውንም አበዙአት።” እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ የኃጥኣንን አንገታቸውን ቈረጠ። ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ። በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥
መዝሙር 128:1-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣ በመንገዱም የሚሄዱ፤ የድካምህን ፍሬ ትበላለህ፤ ብፅዕና እና ብልጽግና የአንተ ይሆናሉ። ሚስትህ በቤትህ፣ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ወንዶች ልጆችህ በማእድህ ዙሪያ፣ እንደ ወይራ ተክል ናቸው። እነሆ፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው፣ እንዲህ ይባረካል። እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ያሳይህ፤ የልጅ ልጅ ለማየትም ያብቃህ።
መዝሙር 128:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔርን የሚፈሩና ትእዛዞቹን በመጠበቅ የሚኖሩ ደስ ይበላቸው። ሠርተህ የምታፈራውን ትመገባለህ፤ ደስታና ሀብትም ታገኛለህ። ሚስትህ በቤትህ እንደ ፍሬያማ የወይን ተክል ትሆናለች፤ ልጆችህም በማእድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ለምለም ቅርንጫፎች ይሆናሉ። እግዚአብሔርን የሚፈራ እንደዚህ የተባረከ ይሆናል። እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ! የኢየሩሳሌምን ብልጽግና በሕይወትህ ዘመን ሁሉ እንድታይ ያድርግህ! የልጆችህን ልጆች ለማየት እንድትበቃ ያድርግህ!
መዝሙር 128:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ጌታን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው። የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፥ ምስጉን ነህ፤ መልካምም ይሆንልሃል። ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፥ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው። እነሆ፥ ጌታን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል። ጌታ ከጽዮን ይባርክህ፥ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ። የልጆችህንም ልጆች ታያለህ። በእስራኤል ላይ ሰላም ይሁን።