መዝሙር 125:1-5
መዝሙር 125:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን። በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን ሞላ፥ አንደበታችንም ሐሤትን አደረገ፤ በዚያን ጊዜ አሕዛብ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው” አሉ። ደስተኞችም ሆን። አቤቱ፥ በአዜብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ። በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይሰበስባሉ።
መዝሙር 125:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በእግዚአብሔር የሚታመኑ፣ ሳትናወጥ ለዘላለም እንደምትኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው። ተራሮች ኢየሩሳሌምን እንደ ከበቧት፣ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ነው። ጻድቃን እጃቸውን ለክፋት እንዳያነሡ፣ የክፉዎች በትረ መንግሥት፣ ለጻድቃን በተመደበች ምድር ላይ አያርፍም። እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም ለሆኑ፣ ልባቸውም ለቀና መልካም አድርግ። ወደ ጠማማ መንገዳቸው የሚመለሱትን ግን፣ እግዚአብሔር ከክፉ አድራጊዎች ጋራ ያስወግዳቸዋል።
መዝሙር 125:1-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሰዎች ከቶ እንደማይነቃነቅና እንደማይናወጥ እንደ ጽዮን ተራራ የጸኑ ናቸው። ተራራዎች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ሆኑ እንዲሁም ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ነው። ክፉዎች በጻድቃን ምድር ላይ የሚዳኙት ለብዙ ጊዜ አይደለም፤ አለበለዚያ ጻድቃንም ክፉ ማድረግን ይጀምራሉ። እግዚአብሔር ሆይ! ትእዛዞችህን ለሚፈጽሙ ደጋግ ሰዎች ቸርነት አድርግላቸው። ነገር ግን ክፉ አድራጊዎችን በምትቀጣበት ጊዜ የአንተን መንገድ የተዉትን ከሐዲዎችንም አብረህ ቅጣቸው።
መዝሙር 125:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በጌታ የታመኑ እንደማይታወክ ለዘለዓለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው። ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ሆኑ፥ ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለም ጌታ በሕዝቡ ዙሪያ ነው። ጻድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ የክፉዎች በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም። አቤቱ፥ ለመልካሞች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ። ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን ዓመፅን ከሚሠሩት ጋር ጌታ ይወስዳቸዋል። ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን።