መዝሙር 123:1-4
መዝሙር 123:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥ የመዓት ቍጣቸውን በላያችን ባነሡ ጊዜ፥ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር ብዬ በተጠራጠርሁ ነበር፥ በውኃ ባሰጠሙን ነበር ብዬ በተጠራጠርሁ ነበር፤
መዝሙር 123:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጥህ ሆይ፤ ዐይኖቼን ወደ አንተ አነሣለሁ። የባሪያዎች ዐይን ወደ ጌታቸው እጅ፣ የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት፣ ምሕረት እስከሚያደርግልን ድረስ፣ የእኛም ዐይኖች ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለከታሉ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ንቀት በዝቶብናልና፣ ማረን፤ እባክህ ማረን። ነፍሳችን የቅንጡዎች ስድብ፣ የትዕቢተኞችም ንቀት እጅግ በዝቶባታል።