መዝሙር 112:1-3
መዝሙር 112:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥ የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ የእግዚአብሔር ስሙ ቡሩክ ይሁን። ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስሙ ይመስገን።
መዝሙር 112:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሃሌ ሉያ። ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ በትእዛዙም እጅግ ደስ የሚሰኝ፤ ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች። ሀብትና ብልጽግና በቤቱ ይሞላል፤ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።