መዝሙር 109:2-4
መዝሙር 109:2-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር የኀይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል፤ በጠላቶችህም መካከል ትገዛለህ። ቀዳማዊ፦ በኀይል ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን ከአንተ ጋር ነበር፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ። እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ ብሎ፥ እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትምም።
መዝሙር 109:2-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ክፉዎችና አታላዮች፣ አፋቸውን ከፍተውብኛልና፤ በውሸተኛ አንደበት ተናግረውብኛል። በጥላቻ ቃል ከብበውኛል፤ ያለ ምክንያትም ጥቃት አድርሰውብኛል። ስወድዳቸው ይወነጅሉኛል፤ እኔ ግን እጸልያለሁ።