መዝሙር 105:16-19
መዝሙር 105:16-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሙሴንም፥ እግዚአብሔር የቀደሰውን አሮንንም በሰፈር አስቈጧቸው። ምድር ተከፈተች፥ ዳታንንም ዋጠችው፥ የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፤ በማኅበራቸው እሳት ነደደች፥ ነበልባልም ኃጥኣንን አቃጠላቸው። በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።
መዝሙር 105:16-19 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በምድሪቱ ላይ ራብን ጠራ፤ የምግብንም አቅርቦት ሁሉ አቋረጠ፤ በባርነት የተሸጠውን ሰው፣ ዮሴፍን ከእነርሱ አስቀድሞ ላከ። እግሮቹ በእግር ብረት ተላላጡ፤ በዐንገቱም የብረት ማነቆ ገባ። የተናገረው ቃል እስኪፈጸምለት፣ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው።