መዝሙር 102:1-3
መዝሙር 102:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነፍሴ፥ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች። አጥንቶቼም ሁሉ የተቀደሰ ስሙን። ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትረሳም። ኀጢአትህን ሁሉ ይቅር የሚልልህ፤ ደዌህንም ሁሉ የሚፈውስህ፥
መዝሙር 102:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ። በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ መልስልኝ። ዘመኔ እንደ ጢስ ተንኖ ዐልቋልና፤ ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል።