ምሳሌ 4:7-9
ምሳሌ 4:7-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ። ጠብቃት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አክብራት፥ እርስዋም ታቅፍሃለች። ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፥ በደስታ አክሊልም ትጠብቅሃለች።
ያጋሩ
ምሳሌ 4 ያንብቡምሳሌ 4:7-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ጥበብ ታላቅ ነገር ናት፤ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፤ ያለህን ሁሉ ብታስከፍልህም ማስተዋልን ገንዘብህ አድርጋት። ክብርን ስጣት፤ ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ ዕቀፋት፤ ታከብርሃለች፤ በራስህ ላይ ሞገሳማ አክሊል ትደፋልሃለች፤” የክብር ዘውድም ታበረክትልሃለች።
ያጋሩ
ምሳሌ 4 ያንብቡምሳሌ 4:7-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ጥበብ ከሁሉ በላይ ስለ ሆነች እርስዋን ገንዘብ አድርግ፤ ያለህን ሁሉ ቢያስከፍልህም ማስተዋልን ለማግኘት ትጋ። ጥበብን አክብራት፤ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አጥብቀህም ብትይዛት፥ ክብርን ትሰጥሃለች። የክብርን አክሊል ታቀዳጅሃለች፤ የተዋበውንም ዘውድ ትሰጥሃለች።”
ያጋሩ
ምሳሌ 4 ያንብቡ