ምሳሌ 26:9-12 - Compare All Versions
ምሳሌ 26:9-12 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
በሞኞች አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣ በሰካራም እጅ እንዳለ እሾኽ ነው። ሞኝን ወይም የትኛውንም ዐላፊ አግዳሚ የሚቀጥር፣ ፍላጻውን በነሲብ እየወረወረ ወገኖቹን እንደሚያቈስል ቀስተኛ ነው። ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ሁሉ፣ ሞኝም ቂልነቱን ይደጋግማል። ራሱን እንደ ጠቢብ የሚቈጥረውን ሰው አይተሃልን? ከርሱ ይልቅ ለሞኝ ተስፋ አለው።
ያጋሩ
ምሳሌ 26 NASVምሳሌ 26:9-12 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
የሞኝ በምሳሌ መናገር ሰካራም በእጁ ላይ የተሰካውን እሾኽ ለማውጣት እንደ መታገል ያለ ነው። በመንገድ የሚተላለፉትን ሞኞች ወይስ ሰካራሞች ሁሉ የሚቀጥር አሠሪ ያገኘውን ሰው ሁሉ እንደሚያቈስል ቀስት ወርዋሪ ነው። ሞኝነቱን ደጋግሞ የሚገልጥ ሞኝ ሰው ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ውሻ ነው። በራሱ አስተሳሰብ ጠቢብ የሆነ ከሚመስለው ሰው ይልቅ ሞኝ ሰው ተስፋ አለው።
ያጋሩ
ምሳሌ 26 አማ05ምሳሌ 26:9-12 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
በሞኝ የሚነገር ምሳሌ፥ በሰካራም እጅ እንዳለ እሾኽ ነው። ሞኝን ወይንም አላፊ አግዳሚውን የሚቀጥር ሰው ነው፥ ሁሉን እንደሚያቆስል አዳኝ ነው። ወደ ሞኝነቱ የሚመለስ ሰው፥ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ውሻ ነው። ለራሱ ጠቢብ የሆነ የሚምስለውን ሰው አየኽውን? ከእርሱ ይልቅ ሞኝ ተስፋ አለው።
ያጋሩ
ምሳሌ 26 መቅካእኤ