ምሳሌ 22:22-23 - Compare All Versions
ምሳሌ 22:22-23 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ድሃን በግድ አትበለው፥ ድሃ ነውና ችግረኛውንም በበር አትግፋው፤ እግዚአብሔር ፍርዱን ይፈርድለታልና። አንተም ነፍስህን በሰላም ታድናለህ።
ምሳሌ 22:22-23 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ድኾች በመሆናቸው ብቻ ድኾችን አትበዝብዛቸው፤ ችግረኛውንም በአደባባይ አታንገላታው፤ እግዚአብሔር ይፋረድላቸዋልና፤ የሚቀሟቸውንም ይቀማቸዋል።
ያጋሩ
ምሳሌ 22 NASVምሳሌ 22:22-23 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ምንም ስለሌላቸው፥ ድኾችን አትበዝብዝ፤ የተጨቈኑትንም ሰዎች በፍርድ ሸንጎ አታጒላላ፤ ይኸውም እግዚአብሔር ስለሚከራከርላቸውና የሚያስጨንቁአቸውንም ስለሚያስጨንቅ ነው።
ያጋሩ
ምሳሌ 22 አማ05ምሳሌ 22:22-23 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ድሀን አትግፈፈው ድሀ ነውና፥ ችግረኛውንም በበር አትጨቁነው፥ ምክንያቱም ጌታ ለእነርሱ ይሟገታልና፥ የቀሙአቸውንም ሰዎች ሕይወት ይቀማልና።
ያጋሩ
ምሳሌ 22 መቅካእኤ