ምሳሌ 2:7-9
ምሳሌ 2:7-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እርሱ ቅንነትን ለሚያደርጉ ደኅንነትን ያከማቻል፤ በመንገዳቸውም ይቆምላቸዋል። የጽድቅን ጎዳና ይጠብቃል፤ የሚፈሩትንም መንገድ ያጸናል። የዚያን ጊዜ ጽድቅንና ፍርድን ታውቃለህ፤ መልካም መንገድንም ሁሉ ታቃናለህ።
ያጋሩ
ምሳሌ 2 ያንብቡምሳሌ 2:7-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እርሱ ለቅኖች ትክክለኛ ጥበብ ያከማቻል፤ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱትም ጋሻ ይሆናቸዋል፤ የፍትሕን መንገድ ይጠብቃል፤ የታማኞቹንም አካሄድ ያጸናል። በዚያ ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትሕን፣ ሚዛናዊነትን፣ መልካሙንም መንገድ ሁሉ ትገነዘባለህ፤
ያጋሩ
ምሳሌ 2 ያንብቡምሳሌ 2:7-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እርሱ ለቀጥተኞች መልካም ጥበብን ይሰጣል፤ በተግባራቸው ነቀፋ ለሌለባቸው ጋሻቸው ነው። የፍትሕን ሂደት ይከታተላል፤ በታማኝነት የሚያገለግሉትንም ይጠብቃል። እኔ የምልህን ሁሉ ብትሰማ፥ ቀጥተኛ፥ ትክክልና ቅን የሆነውን መንገድ ትገነዘባለህ፤ ልታደርገው የሚገባህንም መልካም ነገር ሁሉ ታውቃለህ።
ያጋሩ
ምሳሌ 2 ያንብቡ
