ፊልጵስዩስ 4:6-11

ፊልጵስዩስ 4:6-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በም​ንም አት​ጨ​ነቁ፤ ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማል​ዱም፤ እያ​መ​ሰ​ገ​ና​ች​ሁም ልመ​ና​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጡ። ሁሉ የሚ​ገ​ኝ​ባት፥ ከል​ቡ​ናና ከአ​ሳብ ሁሉ በላይ የም​ት​ሆን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ልባ​ች​ሁ​ንና አሳ​ባ​ች​ሁን ታጽ​ናው። አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እው​ነ​ትን ሁሉ፥ ቅን​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ ጽድ​ቅ​ንም ሁሉ፥ ንጽ​ሕ​ና​ንም ሁሉ፥ ፍቅ​ር​ንና ስም​ም​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ በጎ​ነ​ትም ቢሆን፥ ምስ​ጋ​ናም ቢሆን፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ አስቡ። ከእኔ የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ት​ንና የተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ትን፥ የሰ​ማ​ች​ሁ​ት​ንና ያያ​ች​ሁ​ት​ንም እነ​ዚ​ህን አድ​ርጉ፤ የሰ​ላም አም​ላ​ክም ከሁ​ላ​ችሁ ጋር ይሆ​ናል። በጌ​ታ​ችን እጅግ ደስ አለኝ፤ ቢሳ​ና​ችሁ እንኳ አሁ​ንም እን​ደ​ም​ታ​ስ​ቡ​ልኝ፥ ከዱሮ ጀምሮ ለእኔ ችግር ታስቡ፥ ትተ​ጉም ነበ​ርና። ይህ​ንም የምል ስለ አጣሁ አይ​ደ​ለም፤ ያለኝ እን​ደ​ሚ​በ​ቃኝ አው​ቃ​ለ​ሁና።

ፊልጵስዩስ 4:6-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ ከምስጋናም ጋራ ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም፣ ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ። ከእኔ የተማራችሁትን ወይም የተቀበላችሁትን፣ የሰማችሁትን ወይም ያያችሁትን ማንኛውንም ነገር አድርጉ፤ የሰላም አምላክም ከእናንተ ጋራ ይሆናል። ከብዙ ጊዜ በኋላ እንደ አዲስ ስለ እኔ ማሰብ በመጀመራችሁ፣ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ በርግጥ በተግባር ለመግለጽ ዕድሉ አልነበራችሁም እንጂ ማሰቡንስ ታስቡልኝ ነበር። ይህን የምለው ስለ ቸገረኝ አይደለም፤ ምክንያቱም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን፣

ፊልጵስዩስ 4:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል። ነገር ግን አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ ጊዜ አጣችሁ እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር። ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና።

ፊልጵስዩስ 4:6-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ስለዚህ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፥ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ። ከሰው ማስተዋል ሁሉ በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አእምሮአችሁን በኢየሱስ ክርስቶስ ይጠብቃል። አእምሮአችሁ በእነዚህ ከሁሉ በሚበልጡና በሚያስመሰግኑ መልካም ነገሮች የተመላ ይሁን፤ በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ፥ ክቡር፥ ትክክለኛ፥ ንጹሕ፥ አስደሳችና ምስጉን የሆኑ ነገሮችን ሁሉ አስቡ። ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን፥ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ሁሉ አድርጉ፤ የሰላም አምላክም ከእናንተ ጋር ይሆናል። ከብዙ ጊዜ በኋላ እንደገና ለእኔ ችግር ማሰብ ስለ ጀመራችሁ በጌታ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፤ ይህንንም ስል የአሰባችሁትን በሥራ ለማሳየት መልካም አጋጣሚ አላገኛችሁም ነበር ማለቴ ነው እንጂ ስለ እኔ ችግር ማሰባችሁን አቋርጣችኋል ማለቴ አይደለም። ደግሞም ይህን የምለው ለኑሮዬ የሚያስፈልገኝን በማጣቴ አይደለም፤ እኔማ “ያለኝ ነገር ይበቃኛል” ማለትን ተምሬአለሁ።

ፊልጵስዩስ 4:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በምንም ዓይነት ነገር አትጨነቁ። ከሰውም ማስተዋል ሁሉ በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ክቡር የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ምስጉን የሆነውን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም ሁሉ አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል። ነገር ግን አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደገና ማሰብ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ተሰኝቻለሁ፤ አጋጣሚዎች አልተመቻቹላችሁም እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር። ይህን ስል ስለሚያስፈልገኝ ነገር እያማረርሁ አይደለም፤ ያለኝ ነገር ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና።

ፊልጵስዩስ 4:6-11

ፊልጵስዩስ 4:6-11 NASVፊልጵስዩስ 4:6-11 NASVፊልጵስዩስ 4:6-11 NASVፊልጵስዩስ 4:6-11 NASVፊልጵስዩስ 4:6-11 NASVፊልጵስዩስ 4:6-11 NASV