ፊልጵስዩስ 4:21-22
ፊልጵስዩስ 4:21-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳንን ሁሉ ሰላም በሉ፤ በእኔ ዘንድ ያሉ ወንድሞቻችንም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። ቅዱሳንም ሁሉ፥ ይልቁንም ከቄሣር ቤተ ሰብእ የሆኑ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
ፊልጵስዩስ 4:21-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ለቅዱሳን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእኔ ጋራ ያሉት ወንድሞችም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። ቅዱሳን ሁሉ፣ በተለይም ከቄሳር ቤተ ሰው የሆኑት ወገኖች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
ፊልጵስዩስ 4:21-22 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ለቅዱሳን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ሰላምታ አቅርቡ። ከእኔ ጋር ያሉቱ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። ቅዱሳን ሁሉ ይልቁንም ከቄሣር ቤት የሆኑቱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።