ፊልጵስዩስ 3:10-11
ፊልጵስዩስ 3:10-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በእርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን አውቀዋለሁ፤ የመነሣቱንም ኀይል በሕማሙ እሳተፈዋለሁ፤ በሞቱም እመስለዋለሁ። ይኸውም ሙታን በሚነሡ ጊዜ ምናልባት በዚህ አገኘው እንደ ሆነ ብዬ ነው።
ፊልጵስዩስ 3:10-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ክርስቶስንና የትንሣኤውን ኀይል እንዳውቅ፣ በሥቃዩ ተካፋይ እንድሆንና በሞቱም እርሱን እንድመስል እመኛለሁ፤ ለሙታን ትንሣኤም እንድደርስ እናፍቃለሁ።
ፊልጵስዩስ 3:10-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።