ፊልጵስዩስ 2:12-18

ፊልጵስዩስ 2:12-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙኝ ሳለሁ ብቻ ሳይ​ሆን፥ ሳል​ኖ​ርም በፍ​ር​ሀ​ትና በመ​ን​ቀ​ጥ​ቀጥ ሆና​ችሁ ለድ​ኅ​ነ​ታ​ችሁ ሥሩ። ለሚ​ወ​ደው ሥራ የሚ​ረ​ዳ​ችሁ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታ​ውን ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ። የም​ት​ሠ​ሩ​ትን ሁሉ ያለ ማን​ጐ​ራ​ጐ​ርና ያለ መጠ​ራ​ጠር በፍ​ቅ​ርና በስ​ም​ም​ነት ሥሩ። እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ንጹ​ሓ​ንና የዋ​ሃን ትሆኑ ዘንድ፥ በማ​ያ​ም​ኑና በጠ​ማ​ሞች ልጆች መካ​ከል ነውር ሳይ​ኖ​ር​ባ​ችሁ በዓ​ለም እንደ ብር​ሃን ትታ​ያ​ላ​ችሁ፤ የሕ​ይ​ወ​ትን ቃል እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ችሁ፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን እኔ እን​ድ​መካ፤ የሮ​ጥሁ በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና፤ የደ​ከ​ም​ሁም በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና። ስለ ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ሁም የአ​ም​ልኮ መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ። እነ​ሆም እኔ በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤ እና​ን​ተም በእኔ ደስ ይበ​ላ​ችሁ። ከእ​ኔም ጋር ሐሤት አድ​ርጉ።

ፊልጵስዩስ 2:12-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ወዳጆቼ ሆይ! እኔ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ሁልጊዜ ታዛዦች እንደ ነበራችሁ፥ ይልቁንም አሁን ከእናንተ በራቅሁበት ጊዜ ይበልጥ ታዛዦች እንድትሆኑ አሳስባችኋለሁ፤ ስለዚህ እያንዳንዳችሁ መዳናችሁን ፍጹም ለማድረግ በፍርሃትና በአክብሮት ተግታችሁ ሥሩ። እግዚአብሔር ታዛዥነትን ለእናንተ እየሰጠ ዓላማውን ከፍጻሜ ለማድረስ በእናንተ ውስጥ ይሠራል። ማናቸውንም ሥራ በምትሠሩበት ጊዜ አታጒረምርሙ ወይም አትከራከሩ። ይህም ከሆነ በዚህ በጠማማና በመጥፎ ትውልድ መካከል ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ንጹሓን የእግዚአብሔር ልጆች በመሆን በዚህ ዓለም እንደ ከዋክብት ታበራላችሁ። ይህም የሚሆነው ሕይወት የሚገኝበትን ቃል ሳታቋርጡ አጥብቃችሁ በመያዝ ነው፤ በዚህ ዐይነት ሩጫዬም ሆነ ሥራዬ ከንቱ ሆኖ ስለማይቀር ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ የምመካበት ምክንያት ይኖረኛል ማለት ነው። ለእግዚአብሔር በእምነት በምታቀርቡት መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ የእኔም ሕይወት ተጨማሪ መሥዋዕት ሆኖ ቢቀርብ እንኳ ደስ ይለኛል፤ እናንተም የደስታዬ ተካፋዮች ትሆናላችሁ። እንዲሁም እናንተ ተደስታችሁ እኔንም የደስታችሁ ተካፋይ ታደርጉኛላችሁ።

ፊልጵስዩስ 2:12-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ ይበልጥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ በጎ ፈቃዱን እንድትፈልጉና እንድታደርጉ ሁለቱንም በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። ሁሉንም ነገሮች ሳታጉረመርሙና ሳትከራከሩ አድርጉ፤ በዚህም በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ሆናችሁ በዚህ ዓለም እንደ ከዋክብት የምታበሩ፥ ያለ ነቀፋ የዋሆችና ነውርም የሌለባችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ፤ እናንተም የሕይወትን ቃል በጽኑ በመያዛችሁ ምክንያት በከንቱ እንዳልሮጥሁ በከንቱም እንዳልደከምሁ በክርስቶስ ቀን የምመካበት ነገር ይሆንልኛል። ነገር ግን በእምነታችሁ በምታቀርቡት መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ እንደ መጠጥ ቊርባን ብፈስስ ደስ ይለኛል፤ ከእናንተም ከሁላችሁ ጋር አብሬ ሐሤት አደርጋለሁ፤ እናንተም ደግሞ እንዲሁ ደስ ይበላችሁ፤ ከእኔም ጋር አብራችሁ ሐሤት አድርጉ።

ፊልጵስዩስ 2:12-18

ፊልጵስዩስ 2:12-18 NASVፊልጵስዩስ 2:12-18 NASVፊልጵስዩስ 2:12-18 NASVፊልጵስዩስ 2:12-18 NASVፊልጵስዩስ 2:12-18 NASVፊልጵስዩስ 2:12-18 NASV